​ኮስታዲን ፓፒች ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ወደ አዲግራት አልተጓዙም

የኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ኮስታዲን ፓፒች በቤተሰብ ጉዳይ ምክንያት ኢትዮጵያ ቡና ከወልዋሎ የሚያደርገውን ጨዋታ እንደማይመሩ ታውቋል።

ፓፒች አባታቸው ባጋጠማቸው ህመም ምክንያት ወደ ትውልድ ሀገራቸው እንደሚጓዙ የታወቀ ሲሆን ቡድኑ ከወልዋሎ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ወደ አዲግራት ሲጓዝ ከቡድኑ ጋር አብረው አልተጓዙም። የፓፒች ረዳቶች የሆኑት ሐብተወልድ ደስታ እና ቴክኒክ ዳይሬክተሩ በጨዋታው ቡድኑን የሚመሩ ይሆናል፡፡ አሰልጣኙ ምናልባትም የአባታቸው የጤና ሁኔታ በፍጥነት ካልተሻሻለ በሰርቢያ ሊሰነብቱ ይችላሉ ተብሏል።

ኢትዮጵያ ቡና ለእሁዱ ጨዋታ ከዋና አሰልጣኙ ፓፒች በተጨማሪ የቡድን መሪ እና የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ በመሆን እያገለገለ የሚገነው ውብሸት ደሳለኝንም ግልጋሎት አያገኝም። ውብሸት እሁድ ናይጄርያን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ መሆኑ ይታወቃል።

የ57 አመቱ ኮስታዲን ፓፒች በጥቅምት ወር መጨረሻ በህመም ምክንያት ከቡድኑ ጋር የተለያዩት ድራጋን ፖፓዲችን ተክተው የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸው የሚታወስ ሲሆን በ3 ጨዋታ 7 ነጥብ ሰብስቦ በደረጃ ሰንጠረዡ አናት እንዲቀመጥ አስችለውታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *