ፍፁም ገ/ማሪያም ከኤሌክትሪክ ጋር ግንኙነት እንደሌለው አስተባበለ

የቅዱስ ጊዮርጊሱ አጥቂ ፍፁም ገ/ማሪያም ከኤሌክትሪክ ጋር ምንም ዓይነት ድርድር አለማድረጉን ዛሬ ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጠው አስተያየት ገለፀ፡፡ ፍፁም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ቀሪ የአንድ ዓመት ውል ሲኖረው ከየትኛው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለብ ጋር ድርድር አለማድረጉን ጨምሮ ተናግሯል፡፡

ኤሌክትሪክ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በከፍተኛ ደረጃ ስሙ የተያያዘውን የራምኬል ሎክ ተተኪ ሊያደርግው ነው የተባለውም ሀሰት እንደሆነ ተጫዋቹ ለሶከር ኢትዮጵያ አስረድቷል፡፡

“እኔ ለዕረፍት አሜሪካ ነበርኩ፡፡ ከየትኛውም ክለብ ጋር ድርድር አላደረኩም፡፡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋርም የአንድ ዓመት ቀሪ ውል አለኝ፡፡ ቀሪ የውል ጊዜን አከብራለው፡፡ ወደ ኤሌክትሪክ ሊዛወር ነው የሚሉ ወሬዎች በሙሉ ሀሰት ናቸው::” በማለት አስተባብሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *