የፌዴሬሽኑ ምርጫ ​እጣፈንታ ቅዳሜ ይለይለታል

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስመራጭ ጠቅላላ ጉባኤ በተያዘለት ቀን ቅዳሜ ጥር 5 በሰመራ የሚካሄድ ሲሆን ስለምርጫው መካሄድ አለመካሄድ ጥያቄም በቀኑ ምላሽ እንደሚያገኝ ይጠበቃል፡፡

ፊፋ ዛሬ ለፌድሬሽኑ የመንግስት ጣልቃ ግብነት መኖሩን አለመኖሩን መፈተሸ እንዳለበት ያሳሳበበትን ደብዳቤ ከላከ በኃላ የአስመራጭ ኮሜቴ አባላቶች ውጥረት የተሞላበት ስብሰባ አድርገዋል፡፡ እስከምሽት በዘለቀው ስብሰባቸው ምርጫ የማራዘም ስልጣን የኮሚቴው አለመሆኑን የተስማሙ ሲሆን ቅዳሜ በሚደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በተላከው የፊፋ ደብዳቤ እና የምርጫው ቀጣይ ሁኔታ ላይ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡

ፊፋ አፅኖት ሰጥቶ ከሚቃወማቸው እና የተቋቋመበትን መርህ ከሚፈታተኑ ችግሮች ዋነኛው የመንግስት ጣልቃ ገብነት በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ላይ የማያወላውል እርምጃ ሊወስድ ይችላል፡፡

የጥር 5 ምርጫን ተከትሎ ከወዲሁ አዘጋጁ የአፋር ክልል እግርኳስ ፈድሬሽን ከፍተኛ ወጪ በማውጣት እንግዶቹን እየጠበቀ ነው፡፡

አሁን በደረሰን ዜና መሰረት የፌድሬሽኑ አመራሮች ረቡዕ ማለዳ ውይይት እንደሚያደርጉ ተነግሯል። አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የመጠራቱም እድል የሰፋ ነው። አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤው ሰመራ ላይ ወይስ አዲስ አበባ ላይ ይካሄድ የሚለውም ጥያቄ መልስ ነገ ያገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *