​ኢትዮጵያ ቡና ዩጋንዳዊ አጥቂ አስፈርሟል

ኢትዮጵያ ቡና ዩጋንዳዊው የአጥቂ መስመር ተጫዋች ቦባን ዚሪንቱዛን ማስፈረሙ ታውቋል።

በውድድር አመቱ መልካም ያልሆነ ውጤት እያስመዘገበ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና ጠባብ የሆነው የማጥቃት አማራጩን ለማስፋት ዚሩንቱዛን በአንድ አመት ኮንትራት ማስፈረም ችሏል። ክለቡ ተጫዋቹን የውጪ ተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ከመጠናቀቁ በፊት ማስፈረሙ የታወቀ ሲሆን ያለፉትን 3 ቀናት በክለቡ ልምምድ ሲሰራ ቆይቷል።

በተለያዩ የአጥቂ አማራጮች እና በአጥቂ አማካይነት መሰለፍ የሚችለው ቦባን ቦጎሪ ዚሩንቱዛ በሀገሩ ክለቦች ቪላ እና ቫይፐርስ ፣ በዚምባብዌው ዳይናሞስ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካው ፖልክዋኔ ሲቲ እንዲሁም ዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወደ ዛምቢያው ክለብ ቢዩልድኮን በሁለት አመት ኮንትራት ቢያመራም ከ6 ወራት ቆይታ በኋላ ክለቡን ለቆ ወደ ኢትዮጵያ ቡና አምርቷል።

ሰኞ እለት በተጠናቀቀው የውጪ ተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ዚሩንቱዛ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ 5ኛው ተጫዋች ሆኗል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *