ፊፋ የወሩን የሃገራት ደረጃ ይፋ አድርጓል

የፊፋ ኮካ ኮላ የሃገራት ደረጃ የጥር 2018 ወር ደረጃ ዛሬ ይፋ ሆኗል፡፡ በወሩ ምንም አይነት ጨዋታ ያላደረገው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንም ከነበረበት ስድስት ደረጃዎችን አሻሽሏል፡፡

ኢትዮጵያ በውሩ ደረጃ 137ኛ ሆናለች፡፡ በታህሳስ ወር ኢትዮጵያ 143ኛ የነበረች ሲሆን በወሩ 213 ነጥብ አግኝታ ስታገኝ ባለፈው ወር 196 ነጥብ ነበር የሰበሰበችው፡፡ በወሩ ጨዋታ ባታደረግም የደረጃ ማሻሻል አሳይታለች፡፡ ከሴካፋ ዞን ሃገራት አሁንም ዩጋንዳ ቀዳሚ ሃገር ስትሆን ከዓለም 73ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ ኬንያ 105ኛ፣ ሩዋንዳ 116ኛ እና 12 ደረጃዎችን ያሻሻለው ሱዳን 124ኛ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

የዓለም ደረጃን የአለም ቻምፒዮኗ ጀርመን ስትመራ ብራዚል፣ ፖርቹጋል፣ አርጀንቲና እና ቤልጂየም ይከተላሉ፡፡ ከአፍሪካ ቱኒዚያ መሪነቱን ከሴኔጋል ተቀብላለች፡፡ የካርቴጅ ንስሮቹ ከዓለም 23ኛ ሲሆኑ ሴኔጋል 24ኛ ነች፡፡ ግብፅ፣ ሞሮኮ፣ ዲ.ሪ. ኮንጎ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ካሜሮን እና ጋና ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል፡፡ ናይጄሪያ ከዓለም 51ኛ ነች፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *