​ከፍተኛ ሊግ | የዛሬ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 10ኛ ሳምንት ዛሬ ዲላ እና ሰበታ ላይ የተካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተፈፅመዋል።

የነቀምት ከተማ እና ሽረ እንዳስላሴ ጨዋታ ነቀምት ላይ እንዲካሄድ መርሀግብር ወጥቶለት የነበረ ቢሆንም በአቅም ውስንነት አዲስ አባባ ላይ ጨዋታውን ለማድረግ ለፌዴሬሽኑ ያቀረቡት። ጥያቄ ተቀባይነት ቢያገኝም አአ ስታድየም ከጥር 9-22 ምንም አይነት ጨዋታ የማያስተናግድ በመሆኑ ሰበታ ላይ ተካሂዶ ያለ ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

በተቀዛቀዘ ሁኔታ የተጀመረው እና በጉሽሚያ የተሞላው ጨዋታ የጎል ሙከራ ለማስተናገድም በርካታ ደቂቃዎች አስተናግደዋል። በ19ኛው ደቂቃ ልደቱ ለማ ከርቀት መትቶ ወደ ውጪ ከወጣበት እና በ40ኛው ደቂቃ ብሩክ ገብረ አብ ጥሩ የማግባት ዕድል አግኝቶ በግቡ አናት ከሰደዳት ኳስ ውጪ ሙከራ ሳይታይበት የመጀመርያው አጋማሽ ተጠናቋል።

በመጀመሪያው አጋማሽ የዕለቱ ዳኛ የነበሩት አዲሱ አምሳሉ በ21ኛው ደቂቃ የወሰኑት ውሳኔ አስገራሚ ውሳኔ ሆኖ አልፏል። የሸረ ተጫዋች ተጎድቶ ህክምና አግኝቶ የመግባት ጥያቄ በ4ኛው ዳኛ አማካይነት የመግባት ጥያቄ አቅርቦ ከዳኛው እሺታ በገኘበት ቅጽበት ኳሷ ወደ ብሩክ ገብረአብ እግር በማምራት የነቀምትን የመጨረሻ ተከላካይ አልፎ ሲሄድ የእለቱ ዳኛ ጨዋታውን አስቆመው በማሻማት በድጋሚ እንዲጀመር አስደርገዋል፡፡
ከዕረፍት መልስ ነቀምት ከተማ ተጭነው የተጫወቱ ሲሁን የግብ ዕድል በ59ኛው ደቂቃ ላይ ከቀኝ መስመር ላይ ዘነበ ተኔታ ያሻገረውን ኳስ ነፃ አቆቆም ላይ ሁኖ የነበረው አላዛር ዝናቡ ወደ ግብ ለወጠው ሲባል ሳይጠቀምባት ቀርቷል። ነቀምት ከተማዎች ዋቁማ ዲንሳ እና ዝናቡ ኃይሉ ፤ ሽረዎች ደግሞ በልደቱ ለማ እና ብሩክ ገብረዓብ አማካይነት ሙከራ ቢያደርጉም ግብ ሳይቆጠር ጨዋታው ያለ ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

በምድብ ለ መሪው ዲላ ከተማ 08:00 ላይ ሀላባ ከተማን አስተናግዶ 1-1 ተለያይቷል፡፡ በመጀመርያው አጋማሽ ግብ ባልተስተናገደበት ጨዋታ በ60ኛው ደቂቃ ሀላባ ከተማ በአምበሉ አዩብ በቀታ ግብ መሪ መሆን ቢችሉም በ72ኛው ደቂቃ ምትኩ ማሜጫ ዲላ ከተማን አቻ አድርጓል። ዲላ ያለመሸነፍ ጉዞን ለተጨማሪ ሳምንት አርዝሞ መውጣትም ችሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *