የከፍተኛ ሊግ አጫጭር መረጃዎች

ኢትዮጵያ መድን

ኢትዮጵያ መድን ከአስራት ኃይሌ ጋር በተፈጠረው ውዝግብ ምክንያት ከማንኛውም ውድድር መታገዱ ይታወሳል። ሆኖም ኢትዮጵያ መድን ከፌዴሬሽን ጋር ባደረገው ረጅም ሰዓት ስብሰባ እገዳው እንዲነሳ ከስምምነት መድረሳቸው ታውቋል፡፡ በዚህም የተጣለበት እገዳ ተነስቶ የዚህን ሳምንት ጨምሮ በእገዳው ወቅት ሳይጫወታቸው የቀሩ ጨዋታዎች በተስተካካይ መርሃግብር እንደሚካሄዱ ታውቋል።

ተስተካካይ ጨዋታዎች

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በምድብ ሀ እና ለ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይደረጉ የቀሩ ጨዋታዎችን ተስተካካይ መርሃ ግብር ይፋ አድርጓል። ጨዋታዎቹም ከ13ኛው ሳምንት መርሀ ግብር ቀጥሎ ተደርገው ከተጠናቀቁ በኋላ የ14 እና 15ኛ ሳምንት መርሀ ግብር እንደሚቀጥል ታውቋል።

የተስተካካይ መርሀ ግብሩን ጨምሮ ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ | LINK

በተያያዘ ዜና በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት እርስ በእርስ የሚደገረጉ ጨዋታዎች በአዲስ አበባ የሚደረጉ ይሆናል።

ጅማ አባ ቡና

የቀድሞ የጅማ አባ ቡና ተጫዋቾች የደሞዝ ክፍያ እየተከፈለን አይደለም ሲሉ ጥያቄቸውን ለፌደረሽን አቅርብዋል ፡፡ ተጫዋቾቹ ጥያቄያቸውን ለክለቡ ቦርድ ማቅረባቸው የታወቀ ሲሆን ክለቡም ችግሩን  እንደሚፈታ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡

ሀዲያ ሆሳዕና

ሀድያ ሆስዕና የካፋ ቡና አሰልጣኝ ሰብሳቤ ይባስን ለመቅጠር ፍላጎት ቢሳይም አሰልጣኝ ስብስቤ በካፋ ቡና እና የቡድኑ አስተዳደር ደስተኛ እንደሆኑ በመግለፅ ጥያቄውን እንዳልተቀበሉት ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል። በዚህም ሀዲያ ትኩረቱን ወደ ሌሎች አሰልጣኞች አዙሯል።

ናሽናል ሴሜንት

የድሬዳዋው ክለብ ናሽናል ሴሜንት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፕሮግራም ለውጥ መመረሩን ለሶከር ኢትዮጵያ አስታውቋል። ክለቡ ” ፌዴሬሽኑ ለከፍተኛ ሊግ ትኩረት እየሰጠ አይደለም። ቀደም ብሎ የወጣው ፕሮግራም ዕለተ ቅዳሜ ቢሆንም የፕሪምየር ሊጉ መርሃ ግብር በመለወጡ ምክንያት የኛ ጨዋታ ወደ እሁድ መሸጋገሩን አንቀበለውም ” ብሏል።

የመርሀ ግብር ለውጦች

በጥር ወር የሚከበረው አመታዊው የሀላባ ሴራ በአልን ምክንያት በማድረግ ሀላባ ከተማ ከ ቡታጅራ ከተማ ለሐያደረግጉት የነበረው ጨዋታ ወደ ማክሰኞ ሲሸጋገር ነገ ወልቂጤ ላይ ሊደረግ የነበረው የወልቂጤ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና ጨዋታ በፀጥታ ችግር ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ ተሸጋግሯል።

ጅማ አባቡና(በቴዎድሮስ ታደሰ)

በከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ የሚገኘው ጅማ አባቡና በከፍተኛው ሊግ ዘንድሮ ካደረጋቸው ስምንት ጨዋታዎች 13 ነጥቦችን ሰብስቦ በደረጃ ሰንጠረዥ ከመሪው ዲላ ከነማ በስድስት ነጥቦች ዝቅ ብሎ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ቡድኑ ካደረገው ጨዋታ አንፃር በጥሩ ሁኔታ ላይ ቢገኝም በሜዳው በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የደጋፊ ተቃውሞ እየተስተዋለ ይገኛል።

በጉዳዩ ዙርያ ለሶከር ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን የሰጡት የደጋፊ ማህበሩ ተወካይ ስለ ተቃውሞው እንዲህ ብለዋል። ” ተቃውሞ የጀመረው ገና ከመጀመርያው ጨዋታ ጀምሮ ሲሆን የተቃውሞ መንስኤ ክለቡን በክረምቱ አዲስ የተቀላቀሉት አንዳንድ ተጫዋቾችን አቋም ደጋፊዎች ደስተኛ ባለመሆናቸው እንዲሁም የክለቡም አጨዋወት እንደ ከዚህ ቀደሙ ባለመሆኑ ነው። ነገር ግን ከነገሌ ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ በሰላማዊ ሁኔታ ለመቃወም ባነር አሰርተው ወደሜዳ የገቡ ደጋፊዎች የገበሩ ቢሆንም ሁኔታውን በመጠቀም አላስፈላጊ እና ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጭ የሆነ ተቃውሞ ያሰሙ ግለሰቦችም ነበሩ። ስታድየም የገባ ሰው ሁሉ የአባቡና ደጋፊ ነው ማለት አይደለም። በደጋፊ ስም የደጋፊዎችን ስም ለማጥፋት ማንነታቸውን ባልታወቁ ሰዎች ጥረት መደረጉን እንደ ደጋፊ ማህበር እንቃወማለን። ለወደፊቱም ከዚህ ትምህርት በመውሰድ ከደጋፊዎቹ ጋር ለማስተካከል እንሞክራለን። ”

የቡድኑ ተጫዋቾች በሰጡት አስተያየት ” እንደ ቡድን የደረሰብን ተቃውሞ አግባብ አልነበረም። በእርግጥ በአንዳንድ ተጫዋቾች ላይ የሚነሱ የአቋም መውረድ ይታያል ፣ በክረምቱ የዝውውር ወቅት በሌሎች ክለቦች ጥያቄ ቀርቦላቸው ኮንትራት ስላላቸው በክለቡ ባለመለቀቃቸው የተከፉ ተጫዋቾች አሉ። በእነዚህ እና ባለን ክፍተቶች ዙርያ ተወያይተን ጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው።
” በአሰልጣኞች ዙርያ በኛ በኩል ደስተኞች ነን። በውጤቱም ዙርያ ያን ያክል የከፋ አይደለም። የተሸነፍናቸው ጨዋታዎች ከሜዳ ውጭ የሜዳ አለመመቸት አንዳንድ የዳኞች ስህተት ዋጋ አስከፍለውናል። ከዚህ ውጭ ለተቃውሞ የሚጋብዝ ነገር እንደቡድን ያለብን አይመስለንም። ካለም በሰላማዊ መንገድ በሰለጠነ መልኩ ማካሄድ ይቻላል። ” ብለዋል።

የክለቡ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ግርማ ከበደ በበኩላቸው ” ከተቃውሞ ማግስት ተሰብስበን ተወያይተናል። አሰልጣኙ ባስገቡት ደብዳቤ ዙርያ ከፀጥታ ኃይል ጋር በመነጋገር እንዲሁም ለክለቡ የበላይ ጠባቂ እና ለክለቡ ፕሬዝዳንት የጉዳዩን አሳሳቢነት አፅንኦት ሰጥተን ገልፀናል። ከዚህ በኃላ ተመሳሳይ ችግሮች እዳይፈወሙም ከጸጥታ ሀይሎች ጋር በጋራ እሰራለን። ”

የ11ኛ ሳምንት መሀር ግብር

ምድብ ሀ

ምድብ ለ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *