የካፍ ጠቅላላ ጉባኤ ካዛብላንካ ላይ ይካሄዳል

የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌድሬሽን (ካፍ) መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በሞሮኮ ካዛብላንካ ከተማ ዛሬ ያደርጋል፡፡ ከጠቅላላ ጉባኤው አስቀድሞ የካፍ ስራ አስፈፃሚ አባላት ሐሙስ ስብሰባ የተቀመጡ ሲሆን በዛሬው ጠቅላላ ጉባኤ ከፍተኛ ትኩረትን ያገኘውን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መምረጥ ላይ ነው፡፡

በጠቅላላ ጉባኤው ከዓመት በፊት አዲስ አበባ፣ ራባት እና ማናማ ላይ የተደረጉትን ጠቅላላ ጉባኤዎች ቃለ ጉባኤ እንደሚፀድቅ ሲጠበቅ የኦዲት ሪፖርት፣ የዞን እግርኳስ ማህበራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት፣ የዓመቱን በጀት ማፅደቅ፣ አስፈላጊ ከሆነ ኦዲተሮችን መምረጥ እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መምረጥ የጠቅላላ ጉባኤው ዋነኛ አጀንዳዎች ናቸው፡፡

የአዲት ኮሚቴ፣ የካፍ ዲስፕሊን ፓናል፣ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ እና አስተዳደር ኮሚቴ ፕሬዝደንቶችን እና ምክትል ፕሬዝደንቶችንም ጠቅላላ ጉባኤው እንደሚመርጥ ይጠበቃል፡፡ ከአባል ሃገራት የሚነሱ የመተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ሃሰቦችንም ጠቅላላ ጉባኤው እንደሚመክርበት ተገነግሯል፡፡

የአራት የካፍ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫው ላይ ከአንዱ ዞን በስተቀር በሶስቱ ዞኖች አንድ ብቻ እጩዎች ለውድድር ቀርበዋል፡፡ በማዕከላዊ ዞን የሚወዳደሩት የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ተወካይ ፓትሪስ ኤድዋርድ ንጋሶና በሃገራቸው ተጠጥሮ በነበረው የእርስ በእርስ ጦርነት ለተፈፀሙ ወንጀሎች ተጠያቂ በመሆናቸው ወደ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላነት መምጣት የለባቸውም በሚል መቀመጫውን በባንጉዊ ያደረገው የሰብዓዊ መብት ተማጋች ተቋም የሆነው አል ዊሂዳ ተቋውሞውን አቅርቧል፡፡ ንጋሶና በ2013 ፀረ-ባላካ የጦር እንቅስቃሴን በማስተባበር እንደሚወነጀሉ ጎል ድረ-ገፅ ዘግቧል፡፡  እንደኢንተርናሽናል ቢዝነስ ታይምስ ሪፖርት ከሆነ ደግሞ የፀረ-ባላካ እንቅስቃሴ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ሰላም ላይ ጠንቅ እንደሆነ የሚነገርለት ሲሆን በግጭቶች እና ፓለቲካዊ ቀውሱ ምክንያት 1 ሚሊየን የሚሆኑ የሃገሪቱ ዜጎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው ለመሰደድ ተገደዋል፡፡ ይህንን ተከትሎም ንጋሶና በእጩነት መቅረባቸው የካፍ ፕሬዝደንት አህመድ አህመድን አስተችቶቷል፡፡

ለካፍ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት የሚወዳደሩ እጩዎች

ሰሜን ዞን

ወጪ አባል – ታሪቅ ቦሻማዊ (ቱኒዚያ)

እጩ – ጃማል ኤል-ጃፍሪ (ሊቢያ)

 

ምዕራብ ዞን 1

ወጪ አባል – አልማማይ ካቤሌ ካማራ (ጊኒ)

እጩ – ኦገስቲን ሰንጋሆር (ሴኔጋል)

 

ምዕራብ ዞን 2

ወጪ አባል – ክዌሲ ናያታቺ (ጋና)

እጩ – ሲታ ሳንጋሬ (ቡርኪና ፋሶ)

 

ማዕከላዊ ዞን

ወጪ አባል –ኮንስታንት ኦማሪ ሰልማኒ (ዲ.ሪ. ኮንጎ)

እጩዎች – ፓትሪስ ኤድዋርድ ንጋሶና (የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ)

             ፒየር አሊየን ሞንጉንጊ (ጋቦን)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *