​ጅማ አባጅፋር ጋናዊ አማካይ አስፈርሟል

በፕሪምየር ሊጉ የመጀመርያ የውድድር አመቱ መልካም ጉዞ እያደረገ የሚገኘው ጅማ አባጅፋር ጋናዊው አማካይ አሮን አሞሀን ማስፈረሙን ክለቡ አስታውቋል።

የ24 አመቱ የቀድሞ የአሻንቲ ጎልድ እና ድሪመርስ እንዲሁም በጋና ከ17 እና 20 አመት ቡድኖች የተጫወተው አማካይን ጅማ ከጋና አስመጥቶ በፌዴሬሽን በማስመዝገብ ለአንድ ወር የቆየ የሙከራ ጊዜ የሰጠው ሲሆን በቆይታው አሰልጣኙን በማሳመኑ የአንድ አመት ኮንትራት እንደተሰጠው የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ኢሳይያስ ጂራ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል። በሁለተኛው ዙር ለክለቡ አገልግሎት መስጠት የሚጀምርም ይሆናል።

በክረምቱ የተሳካ የውጪ ተጫዋቾች ዝውውር ያደረገው ጅማ አባ ጅፋር ከዳንኤል አጄይ ፣ አዳማ ሲሶኮ እና ኦኪኪኦላ አፎላቢ በመቀጠል 4ኛ የውጪ ዜጋ ማስፈረም ችሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *