​ወላይታ ድቻ ከ ወልዲያ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ በፌዴሬሽኑ ወሳኔ ተሰረዘ

በኢትዮዽያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንትሶዶ ላይ እንዲደረግ ፌዴሬሽኑ ባወጣው መርሀግብር መሰረት የካቲት 9 አርብ በ09:00 ላይ ጨዋታው እንዲከናወን ለክለቦቹ በደብዳቤ ተገልፆ የጨዋታ አመራሮችም ተመድበው የነበረ ቢሆንም ፌዴሬሽኑ ጨዋታውን ሰርዞታል።

ወልዲያዎች ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ ወደ ወላይታ ሶዶ በማቅናት በአሁን ሰአት በሶዶ ከተማ ንጋት ሆቴል ማረፊያቸውን አድርገው ሲገኙ በአንፃሩ ወላይታ ድቻ ከዛንዚባር ትላንት ማምሻውን አዲስ አበባ በመግባት በአሁኑ ሰአት በአዲስ አበባ ሐራምቤ ሆቴል ይገኛሉ ።

ለጨዋታው መሰረዝ ፌዴሬሽኑ ለሁለቱም ክለቦች በስልክ ደውሎ እንደነገራቸው ሰምተናል ። ወላይታ ዲቻ  አርብ እንዲከናወን የተወሰነውን ጨዋታ ከዛንዚባሩ ዚማሞቶ ጋር ላለበት ወሳኝ የመልስ ጨዋታ በቂ ዝግጅት ማድረግ እንዲንችል ጨዋታው ሌላ ጊዜ እንዲተላለፍለት ለፌዴሬሽኑ ጥያቄ ያቀረበ መሆኑ ሲታወቅ አወዳዳሪው አካል ለጨዋታው መሰረዝ ምክንያት ወላይታ ድቻ ወደሚጫወትበት ሜዳ ለመሄድ አሁን ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አመቺ አለመሆኑ ጨዋታውን ወደ ሌላ ቀን ለማራዘም እንደተገደደ ገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *