ኢትዮ-ኤሌክትሪክ የሁለት ተጫዋቾቹን ውል አራዝሟል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ውላቸው በዚህ ወር የተጠናቀቀው የተክሉ ተስፋዬ እና ሲሴ አልሀሰንን ኮንትራት አድሷል።

ከ2006 ጀምሮ በክለቡ የሚገኘው ሴራሊዮናዊው የተከላካይ መስመር ተጫዋች ሲሴ አልሀሰን ባለፈው አመት በዚህ ወቅት ውሉን ለአንድ አመት አራዝሞ የነበረ ሲሆን አሁንም ውሉን በአንድ አመት በማደስ እስከ 2011 አጋማሽ በክለቡ የሚቆይ ይሆናል።

አምና የመጀመርያው ዙር በተጠናቀቀበት ወቅት በአንድ አመት ውል ወደ ኤሌክትሪክ ያመራው ተክሉ ተስፋዬ ከቡድኑ መጥፎ አቋም በተቃራኒው መልካም የሚባል አመት እያሳለፈ ይገኛል። ለቀጣዮቹ 18 ወራት በክለቡ ለመቆየት ውሉን ማደሱ ታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *