​ወልዋሎ ሶስት ተጫዋቾችን አስፈረመ

ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ያላቸውን ውል ያቋረጡ ሶስት ተጫዋቾችን ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷል። 

ጸጋዬ ኪዳነማርያምን ከአንድ ሳምንት በፊት በዋና አሰልጣኝነት የቀጠረው ክለቡ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የተለያየው አጥቂው ማናዬ ፋንቱ ፣ ከመቐለ ከተማ የለቀቀው አለምነህ ግርማ እና ከአርባምንጭ ከተማ ጋር የተለያየው ታዲዮስ ወልዴን ወደ ቡድኑ ያመጣ ሲሆን ሦስቱም በአንድ አመት ኮንትራት ነው ቡድኑን የተቀላቀሉት። የዓዲግራቱ ክለብ ካስፈረማቸው ተጫዋቾች መካከል አለምነህ እና ታዲዮስ ከአሰልጣኝ ፀጋዬ ጋር በንግድ ባንክ አብረው የሰሩ ሲሆን በሁለት የተለያዩ ክለቦች ከአሰልጣኙ ጋር አብሮ የሰራው የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ታዲዮስ ለሶስተኛ ጊዜ የሚገናኝ ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *