​አዳማ ከተማ ከአላዛር ፋሲካ ጋር ሲለያይ ጫላ ተሺታን አስፈርሟል

አዳማ ከተማ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ካስፈረመው አላዛር ፋሲካ ጋር በስምምነት ሲለያይ ጫላ ተሺታን በአጭር ጊዜ ውል አስፈርሟል።

አላዛር ፋሲካ ወላይታ ድቻን ከለቀቀ በኋላ በአዳማ ከተማ መደላደል ያልቻለ ሲሆን በርካታ የአጥቂ አማራጭ ባለው ቡድን ውስጥ የመጫወት እድል አለማግኘቱን ተከትሎ ከ6 ወራት የክለቡ ቆይታ በኋላ በስምምነት ተለያይቷል። በቀለጣይም ወደ ሀዋሳ ከተማ ሊያመራ አንደሚችል ተገምቷል።

ጫላ ተሺታ በ2008 የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ባሳየው ድንቅ እንቅስቃሴ የበርካቶችን ቀልብ መግዛት ችሎ የነበረ ቢሆንም ከሰበታ ከተማ ወደ ሲዳማ ቡና ባለፈው አመት በዚህ ወቅት ካመራ ወዲህ እምብዛም የመጫወት እድል ማግኘት ሳይችል ቀርቷል።

ፈጣኑ የመስመር አጥቂ ለአዳማ ከተማ እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ ድረስ ለመጫወት የተስማማ ሲሆን በአንፃራዊነት ከሊጉ ክለቦች በተሻለ ለወጣቶች የመጫወት እድል እየሰጠ በሚገኘው አዳማ ራሱን የማሳየት እድል ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *