​ዮናታን ከበደ ወደ ወላይታ ድቻ አምርቷል

ከቀናት በፊት ከአርባምንጭ ከተማ ጋር በስምምነት የተለያየው ዮናታን ከበደ ወደ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊው ወላይታ ድቻ ማምራቱ ታውቋል።

የመስመር አጥቂው በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወደ አርባምንጭ ከተማ በማምራት በደቡብ ካስቴል ዋንጫ መልካም እንቅስቃሴ ቢያሳይም በሊጉ የተጠበቀውን ያህል ሳይሆን በመቅረቱ በሳምንቱ መጀመርያ ከአዞዎቹ ጋር መለያየቱ የሚታወስ ነው። አሁን ደግሞ ወደ ወላይታ ድቻ በማምራት በአንድ አመት ውል ለክለቡ ለመጫወት ተስማምቷል።

ዮናታን ከበደ በሀዋሳ ከተማ ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ ዳሽን ቢራ ፣ አዳማ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማ ተጫውቶ አሳልፏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *