አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ከሰበታ ከተማ ጋር ተለያዩ

የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ሰበታ ከተማን በውድድር አመቱ መጀመርያ ተረክበው ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለማደግ ፉክክር እያደረጉ የነበሩት አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይተዋል።

የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና አአ ከተማ አሰልጣኝ በሰበታ መልካም ጊዜ እያሳለፉ እንደመገኘታቸው መልቀቃቸው አስገራሚ ቢሆንም አሰልጣኙ ከፕሪምየር ሊግ ክለቦች በተለይም ከመከላከያ የቀረበላቸውን የአሰልጥንልን ጥያቄ በመቀበላቸው ምክንያት ከሰበታ ከተማ ጋር ለመለያየት እንደወሰኑ ተነግሯል። በዛሬው እለት መልቀቂያቸውን የተቀበሉት አሰልጣኝ ስዩም ወደ ጦሩ ለመቀላቀል እንደተቃረቡ እና በቀጣዮቹ ቀናት ቡድኑን ሊረከቡ እንደሚችሉ ተሰምቷል።

በተያያዘ ዜና አሰልጣኝ ምንያምር ጸጋዬ ከመከላከያ አሰልጣኝነታቸው መሰናበታቸው ተረጋግጧል። 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *