ወላይታ ድቻ ተጨማሪ ተጫዋች አስፈርሟል

በሁለተኛው ዙር ጠንክሮ ለመቅረብ በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ እየቀላቀለ የሚገኘው ወላይታ ድቻ የአዳማ ከተማው የመሀል ተከላካይ ወንደሰን ቦጋለን በውሰት ውል እስከ ውድድር ዘመኑ መጨረሻ ድረስ ወደ ክለቡ አምጥቷል፡፡

ወንድወሰን ቦጋለ ከአራት አመት በፊት ከአዳማ ከተማ የተስፋ ቡድን በማደግ በተለይ በ2007 የተሻለ የመሰለፍ እድል ማግኘት ቢችልም ባለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት ጠንካራ የተከላካይ መስመር እና አማራጭ ተጫዋቾች በያዘው አዳማ ከተማ በቂ የመጫወት እድል አለማግኘቱን ተከትሎ ቀሪ የውል ጊዜ እያለው ክለቡን በመልቀቅ እስከ ውድድር ዘመኑ መጨረሻ በሚቆይ ኮንትራት ወላይታ ድቻን ተቀላቅሏል፡፡
ወላይታ ድቻ በዝውውር መስኮቱ በመጠቀም ዮናታን ከበደ እና ታዲዮስ ወልዴን ከአርባምንጭ ከተማ እንዲሁም ፀጋዬ ባልቻን (በውሰት) ከሲዳማ ቡና ከቀናት በፊት ማስፈረሙ የሚታወስ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *