ኮንፌድሬሽን ዋንጫ | የኢትዮጵያ ክለቦች ተጋጣሚዎቻቸውን አውቀዋል

በቶታል ካፍ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ወደ ምድብ ለመግባት የሚደረጉ ጨዋታዎች ዛሬ በተደረገው የእጣ ድልድል ሲታወቁ የኢትዮጵያዎቹ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ወላይታ ድቻም ተጋጣሚዎቻቸውን አውቀዋል፡፡ ካይሮ በሚገኘው ካርል ሪትዝ ሆቴል በተደረው የእጣ ድልድል የኮንፌድሬሽን ዋንጫ ድልድሉን ያወጣው የቀድሞ የግብፅ ብሄራዊ ቡድን እና የዛማሌክ ኮከብ ሃዛም ኢማም ነበር፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኮንጎ ሪፐብለኩ ካራ ብራዛቪል ጋር ሲደለደል ወላይታ ድቻ በአንፃሩ ከታንዛኒያው ያንግ አፍሪካንስ ጋር ተመድቧል፡፡ ከቻምፒየንስ ሊጉ የወረደው ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያውን ጨዋታ በሜዳው ሲያደርግ ወላይታ ድቻ ከሜዳው ውጪ ዳሬ ሰላም ላይ ያንጋን ይገጥማል፡፡ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ከመጋቢት 28 እስከ 30 ባሉት ቀናት ሲደረጉ የመልስ ጨዋታዎች ደግሞ ሚያዚያ 9 እና 10 ላይ እንደሚደረጉ ካፍ አስቀድሞ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ አምና ወደ ቻምፒየንስ ሊጉ ምድብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ግዜ ለመግባት የኮንጎ ሪፐብሊኩን ኤሲ ሊዮፓርድስን የረታ ሲሆን ከ2013 በኃላ ወደ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ምድብ መግባት የዶሊሲውን ክለብ የሊግ ተቀናቃኝ ካራን መርታት ይጠበቅበታል፡፡ በሙሉ ስሙ ክለብ አትሌቲክ ሬኔሳንስ ኤግሎንስ በመባል የሚታወቀው ቡድኑ ወደ ሁለተኛው ማጣሪያ ዙር ለመድረስ የጋናው አሻንቲ ኮቶኮ እና የቱኒዚያውን ቤንጎርዳንን አሸንፏል፡፡

ዛማሌክን በመጣል መላው አፍሪካን ያስደመመው ወላይታ ድቻ ከፊቱ ታላቁ የታንዛኒያ ክለብ ያንግ አፍሪካንስ ተደቅኗል፡፡ ያንጋ ለመጨረሻ ግዜ ከኢትዮጵያ ክለብ ጋር በኮንፌድሬሽን ዋንጫው የተጫወተው በ2011 ነበር፡፡ ደደቢት ዳሬሰላም ላይ ከያንጋ ጋር 4-4 ሲለያይ በመልሱ ጨዋታ 2-0 አሸንፎ የታንዛኒውን ክለብ ከውድድር አስወጥቷል፡፡ ያንጋ ከቻምፒየንስ ሊጉ በቦትስዋናው ታውንሺፕ ሮለርስ ተሸንፎ ወደ ኮንፌድሬሽን ዋንጫው ወርዷል፡፡
ወላይታ ድቻ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈው ወደ ምድብ ማምራት ከቻሉ በኢትዮጵያ የክለቦች ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ይሆናል፡፡
ሙሉ ድልድሉ ይህን ይመስላል 
ዛናኮ (ዛምቢያ) ከ ራጃ ክለብ አትሌቲክ (ሞሮኮ)

ኤኤስ ቪታ ክለብ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) ከ ላ ማንቻ (ኮንጎ ሪፐብሊክ)

ቅዱስ ጊዮርጊስ (ኢትዮጵያ) ከ ካራ ብራዛቪል (ኮንጎ ሪፐብሊክ)

አል ሂላል (ሱዳን) ከ አክዋ ዩናይትድ (ናይጄሪያ)

ጎር ማሂያ (ኬንያ) ከ ሱፐርስፖርት ዩናይትድ (ደቡብ አፍሪካ)

ዩዲ ዶ ሶንጎ (ሞዛምቢክ) ከ አል ሂላል ኦብዬድ (ሱዳን)

ፕላቶ ዩናይትድ (ናይጄሪያ) ከ ዩኤስኤም አልጀር (አልጄሪያ)

ቤድቬስት ዊትስ (ደቡብ አፍሪካ) ከ ኢኒየምባ (ናይጄሪያ) አዱዋና ስታርስ (ጋና) ከ ፎሳ ጁኒየርስ (ማዳጋስካር)

ያንግ አፍሪካንስ (ታንዛኒያ) ከ ወላይታ ድቻ (ኢትዮጵያ)

ጄኔሬሽን ፉት (ሴኔጋል) ከ አርኤስ በርካን (ሞሮኮ)

ሲኤፍ ሞናና (ጋቦን) ከ አል መስሪ (ግብፅ)

አሴክ ሚሞሳስ (ኮትዲቫር) ከ ሲአር ቤሎዝዳድ (አልጄሪያ)

ዊልያምስቪል (ኮትዲቯር) ከ ዴፖርቲቮ ኒፋንግ (ኤኳቶሪያል ጊኒ)

ማውንቴን ኦፍ ፋየር ሚኒስትሪ (ናይጄሪያ) ከ ጆሊባ ኤሲ (ማሊ)

ራዮን ስፖርትስ (ሩዋንዳ) ከ ሲዲ ኮስታ ዶ ሶል (ሞዛምቢክ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *