ፍርዳወቅ ሲሳይ ወደ አዳማ ከተማ አምርቷል

የፕሪምየር ሊጉ ክለብ አዳማ ከተማ በቅርቡ ከሀዋሳ ከተማ ጋር የተለያየው የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ፍርዳወቅ ሲሳይን ማስፈረም ችሏል።

በሀዋሳ ከተማ የመደበኛ ተሰላፊነት እድልን ማግኘት ያልቻለው ፍርዳወቅ በአንደኛው ዙር የመጨረሻ ጨዋታዎች ላይ መጫወት ቢችልም በተጠበቀው ልክ ክለቡን ማገልገል አልቻለም በሚል ምክንያት ቀሪ የ6 ወራት ኮንትራት እያለው በስምምነት አፍርሶ ከሀዋሳ ከተማ ጋር መለዬየቱ የሚታወስ ነው። ፍርዳወቅ ከሀዋሳ ከተለያየ ብዙም ሳይቀሰይ አዳማ ከተማን የተቀላቀለ ሲሆን የ18 ወራት ኮንትራትም ተፈራርሟል። 

በተለያዩ የአጥቂ አማራጮች መጫወት የሚችለው ፍርዳወቅ በአዳማ የአጥቂ መስመር ሰብሮ የመግባት ፈተና የሚጠብቀው ይሆናል። ታፈሰ ተስፋዬ እና አላዛር ፋሲካን የለቀቀው አዳማም በዚሁ መስኮት ካስፈረመው ጫላ ተሺታ ጋር የማጥቃት አማራጩን ማስፋት ችሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *