ኢትዮጵያዊያን ዳኞች የአፍሪካ ውድድሮችን ይመራሉ

በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረጉ የሃገራት እና የክለቦች ውድድሮችን እንዲመሩ ኢትዮጵያዊያን ዳኞች በካፍ ተመርጠዋል፡፡ አርቢትሮቹ የቶታል አፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣሪያ እና የኮንፌድሬሽን ዋንጫ ጨዋታዎችን ነው የሚመሩት፡፡

በቶታል ካፍ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ሉሳካ ላይ የዛምቢያው ዛናኮ የሞሮኮው ራጃ ካዛብላካን የሚያስተናግድበትን ጨዋታ ባምላክ ተሰማ እንዲመራ ተመርጧል፡፡ የባምላክ ረዳት የሆኑት ተመስገን ሳሙኤል እና ክንዴ ሙሴ ሲሆኑ ዳዊት አሳምነው አራተኛ ዳኛ ሆኗል፡፡ ጨዋታው በመጪው ቅዳሜ ይደረጋል፡፡

በአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣሪያ ዛምቢያ እና ታንዛኒያ የሚያደርጉትን የመልስ ጨዋታ ሊዲያ ታፈሰ ትመራለች፡፡ የሊዲያ ረዳቶች የሆኑት ክዊንሲ ቪክቶሪ ከሞሪሺየስ እና ሜሪ ጆግርጌ ከኮትዲቯር ናቸው፡፡

በኮንፌድሬሽን ዋንጫ ምድብ ለመግባት ሁለት የኢትዮጵያ ክለቦች ጨዋታቸውን ቅዳሜ ያደርጋሉ፡፡ ዳሬሰላም ላይ የታንዛኒያው ያንግ አፍሪካንስ ከወላይታ ድቻ የሚያደርጉትን ጨዋታን ናይጄሪያዊያኑ ፈረንዲናንድ አኒቴ እንዲሁም ረዳቶቹ አቤል ባባ እና ኢሳ ኡስማን ሲመሩ አዲስ አበባ ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ካራ ብራዛቪል የሚደርጉትን ጨዋታ የሚመሩት ግብፃዊያን አርቢትሮች ናቸው፡፡ የመሃል አርቢትር ኢብራሂም ኒረዲን ሲሆን ረዳቶቻቸው አብደልፈታህ መሃመድ እና የሱፍ ዋሂድ ናቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *