አርባምንጭ ከተማ ገዛኸኝ እንዳለን አስፈርሟል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ግርጌ ላይ የተቀመጠው አርባምንጭ ከተማ በዝውውር መስኮቱ አራተኛ ተጫዋቹን በማስፈረም ገዛኸኝ እንዳለን ወደ ክለቡ ቀላቅሏል።

የመሀል አማካዩ ገዛኸኝ እንዳለ በደደቢት ሐረር ቢራ እና ሀዋሳ ከተማ ቆይታን ያደረገ ሲሆን ሀዋሳ ከተማን በስምምነት ለቆ ወደ ሰበታ ከተማ አምርቶ በመጫወት ላይ ሳለ ነበር በ2008 ላይ ወደ ፋሲል ከተማ በማምራት ያለፉትን ሁለት አመታት በክለቡ ቆይታን ያደረገው። ገዛኸኝ ከአጼዎቹ ጋር ያለው ኮንትራት ሳይጠናቀቅ ክለቡን በስምምነት በመልቀቅ በአርባምንጭ ከተማ የአንድ ሳምንት የሙከራ ጊዜን ተሰጥቶት በስኬት ካጠናቀቀ በኋላ በ1 አመት ኮንትራት ክለቡን የተቀላቀለ ሲሆን የፈጠራ ችግር የሚስተዋልበትን የቡድኑ የአማካይ ክፍል ያሻሽላል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።

አርባምንጭ ከተማ በውድድር ዘመኑ አጋማሽ የዝውውር መስኮት በረከት አዲሱ፣ ዘካሪያስ ፍቅሬ እና ፍቃዱ መኮንንን አስቀድሞ ማስፈረሙ ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *