በወልዋሎ እና መቐለ ከተማ ጨዋታ ዙርያ ውሳኔ ተላለፈ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 17ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አዲግራት ላይ በወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና መቐለ ከተማ መካከል የተደረገው ጨዋታ በእረፍት ሰአት በተፈጠረ የደጋፊዎች ረብሻ ምክንያት መቋረጡ የሚታወስ ነው፡፡

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን ኮሚቴ ዛሬ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት የእንግዳው ቡድን መቐለ ከተማ ደጋፊዎች ለብጥብጡ መነሻ በመሆናቸው ክለቡ ላይ የ90ሺህ ብር ቅጣት ሲተላለፍ የወልዋሎ ክለብ ላይ ደግሞ የ70 ሺህ ብር ቅጣት ተወስኗል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም መቐለ ከተማ በረብሻው የተጎዱ ግለሰቦችን የህክምና ወጪ እንዲሸፍን ተወስኗል፡፡

ጨዋታው ከተቋረጠበት በኋላ ያለው አጋማሽ እስካሁን ያልተካሄደ ሲሆን መቼ እና የት እንደሚካሄድ የሊግ ኮሚቴው እንዲወስን እንዲሁም ከዓዲግራት ስታድየም በ165 ኪሜ ርቀት ላይ በሚገኝ ስታድየም እንደዲከናወን የተላለፈው ውሳኔ ያሳያል፡፡ ሶከር ኢትዮጵያም ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮቿ ባገኘችው መረጃ መሠረት ጨዋታው ሽረ እንዳስላሴ ላይ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የጨዋታው የመጀመርያ አጋማሽ በወልዋሎ 1-0 መሪነት መጠናቀቁ ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *