ፍፁም ገብረማርያም ወደ መከላከያ አምርቷል

ወደ ወልዲያ ባለመመለሳቸው በክለቡ እገዳ ከተላለፈባቸው በኋላ ለፌዴሬሽኑ ባስገቡት ቅሬታ መሠረት እገዳው እንዲነሳላቸው ከተወሰነላቸው ሶስት ተጫዋቸች መካከል አንዱ የሆነው ፍፁም ገብረማርያም ወደ መከላከያ ማምራቱን ዛሬ አረጋግጧል፡

ኤሌክትሪክን ለቆ በክረምቱ ወልዲያን የተቀላቀለው ፍጹም ክለቡ የጣለበትን የገንዘብ ቅጣት በመክፈል መልቀቂያውን የወሰደ ሲሆን ከድሬዳዋ ከተማ ጋር  ስሙ ተያይዞ ቢቆይም በመጨረሻ በዛሬው እለት ወደ መከላከያ የሚቀላቅለውን ፊርማ ተፈራርሟል፡፡ አጥቂው በ20ኛ ሳምንት መከላከያ ከ አርባምንጭ ከተማ በሚያደርገው ጨዋታ ላይም የጦሩን ማልያ ለብሶ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡

በሁለተኛው ዙር አስልጣኝ ስዩም ከበደን የሾመው መከላከያ ከፍጹም በፊት ዳዊት እስጢፋኖስን ማስፈረሙ የሚታወስ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *