የመከላከያው የመስመር አማካይ ጥላሁን ወልዴ ለኢትዮጵያ ቡና መፈረሙን ክለቡ አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያ ቡና በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ዛሬ እንዳስታወቀው ጥላሁን ለ2 አመታት ለአደገኞቹ ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል፡፡
በመስመር ተከላካይነት ፣ አማካይነት እና መሃል አማካይነት መጫወት የሚችለው ጥላሁን ቡናን ለቆ የሄደው ኤፍሬም አሻሞን ቦታ ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ጥላሁን በኒያላ ፣ በአየር ኃይል ፣ ሙገር እና መከላከያ የተጫወተ ሲሆን ለብሄራዊ ቡድኑም በ2012 የሴካፋ ውድድር ላይ ተጫውቷል፡፡