ሩዋንዳ 2018 | ሉሲዎቹ የሴካፋ ዝግጅታቸውን ነገ ይጀምራሉ

በግንቦት ወር አጋማሽ የሚካሄደው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ላይ የሚካፈለው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለውድድሩ የሚያደርገውን ዝግጅት በነገው እለት ይጀምራል። 

የሉሲዎቹ አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያው የተጠቀመችባቸው ተጫዋቾችን በአመዛኙ ይዛ የምትቀጥል ሲሆን የመጀመርያ ጥሪ ደርሷቸው ኋላ ላይ የተቀነሱት አለምነሽ ገረመው፣ ፅዮን እስጢፋኖስ እና ቤተልሄም ሰማን እንዲሁም እንደአዲስ ጥሪ የደረሳት ታሪኳ በርገና ወደ ስብስቡ ሲካተቱ ዘለቃ አሰፋ፣ ሲሳይ ገብረወልድ፣ ሰርካዲስ ጉታ እና ማርታ በቀለ ካለፈው ስብስብ የተቀነሱ ናቸው።

አሰልጣኝ ሰላም ከ24 ተጫዋቾች ስብስብ መካከል በዝግጅት ወቅት ሊቀነሱ እና ሌሎች ያልተመረጡና በሊጉ ጥሩ አቋም እያሳዩ የሚገኙ ተጫዋቾች ሊተኩ እንደሚችሉ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፃለች።

ለሴካፋ ዝግጅት የተጠሩት ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው

ግብ ጠባቂዎች (3)

አባይነሽ ኤርቄሎ (ሀዋሳ ከተማ) ፣ ንግስት መዓዛ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ታሪኳ በርገና (ጥረት)

ተከላካዮች (8)

መሠሉ አበራ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ፀጋነሽ ተሾመ (ድሬዳዋ ከተማ) ፣ ፅዮን እስጢፋኖስ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ብዙዓየሁ ታደሰ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ቤተልሄም ከፍያለው (ኤሌክትሪክ) ፣ መስከረም ካንኮ (ደደቢት) ፣ ታሪኳ ደቢሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ገነሜ ወርቁ (ጌዴኦ ዲላ)

አማካዮች (7)

ሠናይት ቦጋለ (ደደቢት) ፣ አረጋሽ ከልሳ (አካዳሚ) ፣ ዙሌይካ ጁሀድ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ቤዛዊት ተስፋዬ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ህይወት ደንጊሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ እመቤት አዲሱ (መከላከያ) ፣ አለምነሽ ገረመው (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)

አጥቂዎች (6)

ምርቃት ፈለቀ (ሀዋሳ ከተማ) ፣ ሎዛ አበራ (ደደቢት) ፣ ትዕግስት ዘውዴ (ደደቢት) ፣ ሴናፍ ዋቁማ (አዳማ ከተማ) ፣ ረሂማ ዘርጋ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ቤተልሄም ሰማን (ቅዱስ ጊዮርጊስ)

የውድድሩ መጀመርያ ቀን በይፋ ያልተገለፀው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ በግንቦት ወር አጋማሽ እንደሚጀምር ይጠበቃል። በቀጣይ የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ ከአልጄርያ ጋር ወሳኝ ፍልሚያ ለሚጠብቃት ኢትዮጵያም ውድድሩ ጥሩ መዘጋጃ ይሆንላታል።