ድሬዳዋ ከተማ ለሶስት ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሙከራ እድል ሰጥቷል

ድሬዳዋ ከተማ ለሦስት ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች የሙከራ ጊዜ እየሰጠ መሆኑን በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አስታውቋል።

በውድድር አመቱ በወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ ቡድኑንን ለሚቀጥለው የውድድር ዘመን ለማጠናከር በማሰብ በሆላንድ የተለያዩ ሊጎች የሚጫወቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆላንድ ዜግነት ያላቸውን ሳሙኤል ሀብታሙ ፣ ኖኅ ሀብቴ እና ትንሳኤ አበበን ያስመጣ ሲሆን ከትናትናው ዕለት ጀምሮ የሙከራ ጊዜያቸውን በይፋ ጀምረዋል። በቀጣይ በሙከራ ወቅት በሚያሳዩት ብቃትም የክለቡን አመራሮች ማሳመን የሚችሉ ከሆነ ለድሬዳዋ ከተማ ከሚቀጥለው የውድድር ዘመን ጀምሮ ለመጫወት ፊርማቸውን ያኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

በሆላንድ ሀገር ኑሮውን ያደረገው የቀድሞ ተጫዋች እና የአሁኑ አሰልጣኝ ገነነ መክብብ ሦስቱ ተጫዋቾች ወደ ክለቡ በመምጣት የሙከራ ጊዜ እንዲያገኙ እንዳመቻቸ ክለቡ ገልጿል።