አዳማ ከነማ ራሱን እያጠናከረ ነው

ዘንድሮ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለሱን ያረጋገጠው አዳማ ከነማ ኮንትራት በማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾችን በማዘዋወር ላይ ትኩረቱን አድርጓል፡፡

አዳማ ከነማ ወደ ሊጉ እንዲመለስ ከፍተኛውን ሚና የተወጡት አብዱል ከሪም አባፎጊ እና በረከት አዲሱ ኮንትራት ለማራዘም ተስማምተዋል፡፡ አብዱልከሪም መፈረሙ የተረጋገጠ ሲሆን የበረከት አዲሱ ፊርማም በቀጣዮቹ ቀናት ይረጋገጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አዳማ አምና እንዳደረገው ሁሉ ዘንድሮም ልምድ ባካበቱ ተጫዋቾች ዝውውር ላይ ትኩረቱን አሳርፏል፡፡ የመከላከያው አንጋፋ አማካይ አብርሃም ይስሃቅ ከቀድሞ አሰልጣኙ ጋር በድጋሚ ሊገናኝ ጫፍ የደረሰ ሲሆን ሌላው የመከላከያ አጥቂ በዳሶ ሆራ እና የንግድ ባንኩ አጥቂ አብይ በየነ ዝውውር ተጠናቋል፡፡

የቀድሞው የመድን ፣ ቡና እና ንግድ ባንክ አማካይ አብርሃም ይስሃቅ በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ስር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተጫወተ ሲሆን ከመከላከያ ጋር እንደማይቀጥል ተረጋግጧል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊሱ የመስመር አጥቂ ዮናታን ብርሃኔም ወደ አዳማ ሊዘዋወር በመንገድ ላይ ነው፡፡ የተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በጉዳት ያለፈው ዮናታን ወደ አዳማ ከተዛወረ ከሱ ጋር ተመሳሳይ ታሪክ ካለው በረከት አዲሱ ጋር የፊት መስመሩን ይመራሉ፡፡

:

:

:

ምንጭ – ዛሚ ስፖርት ብሄራዊ (ሬድዮ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *