የዳኞች እና ታዛቢዎች ማኅበር በወልዋሎ ላይ የተወሰነው የቅጣት ማቅለያ ዙርያ ቅሬታውን ገለፀ

ባለፈው ሳምንት በአዲስ መልክ የተዋቀረው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የመጀመርያ ስራው የሆነው የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ላይ የተጣለውን የዲሲፕሊን ቅጣት በመመልከት በውሳኔው ላይ ከፍተኛ ማሻሻያ እንዳደረገ የሚታወስ ነው። 

ከቅጣት ውሳኔዎቹ መካከል በ5 ተጫዋቾች ላይ የተላለፈው የ6 ወራት እና የሁለት ዓመት እገዳ ተነስቶ የአንድ ተጫዋች እገዳ ወደ 1 ዓመት ከፍ እንዲል የተደረገበት የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ ላይ የዳኞች እና ታዛቢዎች ማኅበር ቅሬታ አቅርቧል። 

ማኅበሩ በደብዳቤው ላይ ለውሳኔ ማስረጃነት የቀረበው የውድድር አመራሮች ሪፖርት ላይ ችግር ካለም ባቀረቡት ላይ ተገቢው የእርምት እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል።

ሙሉ ደብዳቤው ይህንን ይመስላል:-

ገጽ 1
ገጽ 2