የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተሻሻለ መርሐ ግብር

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በመጪው እሁድ በሚያከናውነው ምርጫ ምክንያት ቅዳሜ እና እሁድ የሚካሄዱ የ25ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ወደ ማክሰኞ መሸጋገራቸው ይታወሳል።

ሁሉም ጨዋታዎች ማክሰኞ እንደሚደረጉ የወጣው መርሀ ግብር ሲያሳይ ጎንደር ላይ ከሚከናወነው ጨዋታ ውጪ ሁሉም በተለመደው መልኩ ይካሄዳሉ። አጼ ፋሲለደስ ስታድየም ላይ የሚካሄደው ጨዋታ በወቅታዊው የከተማዋ የአየር ሁኔታ ምክንያት ረፋድ ላይ እንዲደረግ ክለቡ ጥያቄ ባቀረበው መሰረት 04:00 ላይ ይካሄዳል።

በአዲሱ መርሐ ግብር መሠረት የቀጣይ ሳምንት ጨዋታዎች የሚከተለውን ይመስላሉ።


ማክሰኞ ግንቦት 28 ቀን 2010

04:00 ፋሲል ከተማ ከ መከላከያ (ጎንደር)

09:00 ድሬዳዋ ከተማ ከ መቐለ ከተማ (ድሬዳዋ)

09:00 ሀዋሳ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና (ሀዋሳ)

09:00 አዳማ ከተማ ከ ኢትየ ኤሌክትሪክ (አዳማ)

09:00 ወላይታ ድቻ ከ ኢትዮጵያ ቡና (ሶዶ)

09:00 ወልዲያ ከ ወልዋሎ (አአ)

09:00 ጅማ አባጅፋር ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (ጅማ)

11:30 ደደቢት ከ አርባምንጭ ከተማ (አአ)