ሲዳማ ቡና ያሰናበታቸው ሁለት የውጪ ተጨዋቾቹን እንዲመልስ ተወስኖበታል

ሲዳማ ቡና የዛሬ ወር በዘንድሮው የውድድር አመት ያስመጣቸውን አሽያ ኬኔዲ እና ማማዱ ኮናቴን እንዳሰናበተ የሚታወስ ነው። ሆኖም የክለቡን ውሳኔ ተከትሎ ለእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ አቤቱታቸውን ያቀረቡት ሁለቱ ተጨዋቾች ጉዳያቸው ታይቶ ውሳኔ አግኝተዋል።

እንደ ዲስፕሊን ኮሚቴው ውሳኔ ክለቡ በሁለቱ ተጨዋቾች ላይ ያሳለፈው የስንበት እርምጃ ከህግ ውጪ በመሆኑ የተሻረ ሲሆን በሰባት ቀናት ውስጥም ደሞዛቸው ተከፍሏቸው ወደ ስራቸው እንዲመለሱ አልያም ውላቸው እስኪጠናቀቅ ድረስ  ክፍያው እየተፈፀመላቸው እንዲቆዩ ወስኗል። ከዚህ በተጨማሪም ክለቡ ደሞዛቸው በግማሽ እንዲቀንስ ያደረገበትን ውሳኔ እንዲነሳ ተደርጓል።

የውሳኔውን ዝርዝር የያዘውን ደብዳቤ ከዚህ በታች ያለውን ይመስላል።