ከፍተኛ ሊግ ሀ | ከአናት የሚገኙ ሦስት ክለቦች ነጥብ ጥለዋል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ 18ኛ ሳምንት ትላንት እና ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች ሲገባደድ በሰንጠረዡ አናት የተቀመጡት ሦስት ክለቦች ድል ማስመዝገብ ሳይችሉ ቀርተዋል።

ለገጣፎ ላይ ባህርዳር ከተማን ያስተናገደው ለገጣፎ ለገዳዲ 1-0 አሸንፏል። ትላንት 09:00 ላይ የጀመረው ጨዋታ በዝናብ በመቋረጡ ምክንያት ቀሪ 30 ደቂቃ ዛሬ 4:00 ተካሂዶ ነበር የተጠናቀቀው።

በመጀመሪያዎቹ 10 ደቂቃዎች ባህር ዳሮች በኳስ ቁጥጥርም ሆነ ወደ ተቃራኒ ቡድን የግብ ክልል በመቅረብ የተሻሉ ነበሩ። በተለይ ከቀኝ መስመር ሚኪያስ መኮንን እንዲሁም አምበሉ ደረጀ በረጅሙ ሲያሻግሯቸው የነበሩ ኳሶች አደጋ ሲፈጥሩ ተስተውሏል። ጨዋታው 10 ደቂቃ ከተሻገረ በኋላ ለገጣፎ የበላይነት መውሰድ ሲጀምሩ በርካታ ሙከራም አድርገዋል። በ20ኛው ደቂቃ ሳዲቅ ተማም በቀኝ መስመር ያሻማውን ኳስ ፋሲል አስማማው በግንባሩ ገጭቶ ግብ ጠባቂው ምንተስኖት ሲያድንበት በ28ኛው ደቂቃ በድጋሚ ፋሲል አስማማው ያገኘውን ኳስ በአግባቡ ተቆጣጥሮ ወደ ግብ አክርሮ የመታውን ኳስ   ከባህርዳር ከተማ ግብ ጠባቂ እጅ ብታመልጥም ተከላካዩ ዳግማዊ ሙሉጌታ ደርሶ ከግብነት አድኖታል። በ31ኛው ድቂቃ በሱፍቃድ ነጋሽ  ያሻገረውን ኳስ ፋሲል አስማማው በግንባሩ ገጭቶ ግብ ጠባቂው ያደነበትም ሌላው ተጠቃሽ መለከራ ነበር። በ39ኛው ደቂቃ ተጭነው ሲጫወቱ ለነበሩት ለገጣፎዎች መሪ የምታደርገውን ኳስ ፋሲል አስማማው ከሐብታሙ ፍቃዱ የተሻገረትን ኳስ መሬት ለመሬት በመምታት አስቆጥሯል።

ከዕረፍት መልስ በመጠነኛ ዝናብ በተጀመረው ጨዋታ ባህር ዳር ከተማዋች ውጤቱን ለመለወጥ ተጭነው የተጫወቱ ሲሆን በሙሉቀን ታሪኩ እና ሳለአምላክ ተገኝ የሞከሯቸው ሁለት ሙከራዎች በግብ ጠባቂው እና በተከላካዩ መዝገቡ ቶላ ጥረት ከሽፈዋል። በዕለቱ የነበረው የአየር ንብረት ከፍተኛ ዝናብ በመጣሉ የዕለቱ ጨዋታ ሁለተኛ አጋማሽ ለ15ደቂቃዎች ከተካሄደ በኋላ የተቋረጠ ሲሆን በወቅቱ ጨዋታውን ለመቀጠል አዳጋች በመሆኑ ወደ ዛሬ ረፋድ ለመሸጋገር ተገዷል።

ዛሬ 05:10 ላይ ከተቋረጠበት 60ኛው ደቂቃ የጀመረው ጨዋታ ከፍተኛ የሆነ ጉሽሚያ የታየበት ሲሆን እስከመጨረሻዎቹ 10 ደቂቃዎች ድረስ ምንም አይነት የግብ ሙከራ ያልታየበት ነበር። በ85ኛው ደቂቃ ባህር ዳር ከተማን አቻ የምታደርግ የግብ ዕድል በመልሱ ማጥቃት የተፈጠረለት ሙሉቀን ታሪኩ በአግባቡ ተቆጣጥሮ  ወደፊት በመግፋት የግብ ጠባቂውን አቋቋም ሳይመለከት የመታት ኳስ በቀላሉ በግብ ጠባቂው ድኖበታል። በ90ኛው ደቂቃ ደግሞ መላኩ አበበ ያገኘውን አጋጣሚ ወደግብ ለወጠው ተብሎ ቢጠበቅም ግብ ጠባቂው ምንተሰኖት አሎ ያዳነበት ሙከራ እና በተጨማሪው ደቂቃ በሱፍቃድ ነጋሽ የተሰጠውን ቅጣት ምት በማዘገየቱ በሁለት ቢጫ ከሜዳ የወጣበት ክስተቶች በለገጣፎ በኩል ተጠቃሾች ናቸው።

ትላንት የተካሄዱ ጨዋታዎች ውጤቶች የሚከተሉት ናቸው:-