ሙገር ሲሚንቶ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ ለሱሉልታ ከነማ ድንቅ ብቃት ያሳየው ተከላካዩ በረከት ሳሙኤልን አስፈረመ፡፡
የአሰልጣኝ ግርማ ኃ/ዮሃንስ ሙገር እምቅ ችሎታ ያላቸው ተጫዋቾችን በዝቅተኛ ገንዘብ ማስፈረሙን ቀጥሎበታል፡፡ ክለቡ የበርካታ ተጫዋቾችን ኮንትራት እስከ 300ሺህ ብር በሚደርስ ክፍያ ያራዘመ ሲሆን የለቀቁትን ተጫዋቾች ክፍተት ለመድፈን እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡
በአካል ብቃቱ ገዘፍ ያለው በረከት በባህርዳር በተካሄደው ውድድር ሱሉልታ ከነማ 3ኛ ደረጃ እንዲያገኝ የረዳ ሲሆን በውድድሩ በብዙዎች የተወደሰው የሱሉልታ ከነማ የተከላካይ ክፍል መሪ ነበር፡፡
ሙገር ሲሚንቶ ተጫዋቹን ለሁለት የውድድር ዘመን ለማስፈረም 100,000 ብር ወጪ አድርጓል፡፡