ሩሲያ 2018 | ባምላክ ተሰማ አራተኛ አርቢትር የሆነበት ጨዋታ ነገ ይደረጋል

ሐሙስ የተጀመረው የፊፋ የዓለም ዋንጫ በምድብ ጨዋታዎች ቀጥሎ እየተደረገ ይገኛል። አፍሪካን ከወከሉት አርቢትሮች መካከል የሆነው ኢንተርናሽናል አርቢትር ባምላክ ተሰማ ነገ የሚደረግ አንድ ጨዋታ ላይ ከሚመሩ ዳኞች መካከል አንዱ ሆኗል።

ፊፋ የጨዋታ አርቢትሮችን ዝርዝር ዓርብ ምሽት ይፋ ሲያደርግ በምድብ 5 ኮስታ ሪካ ከሰርቢያ በሚያደርጉት ጨዋታ ላይ ባማላክ አራተኛ ዳኞ ሆኖ ተሹሟል። ጨዋታን ሴኔጋላዊው ማላንጋ ዴይዴሆ በመሃል ዳኛነት ሲመራ ምክትሎቹ ጅብሪል ካማራ እና ኤል ሃጂ ሳምባ ሁነዋል። ሩሲያዊው ቲኮን ካሉጂን በተጠባባቂነት ተይዟል። ጨዋታው በሳማራ አሬና ይደረጋል።

ባምላክ በቀጣይ ጨዋታዎች ላይ በመሃል አርቢትርነት እንደሚሾም ይጠበቃል።