ሲሸልስ አዲስ አሰልጣኝ ሹማለች

የሲሸልስ እግርኳስ ፌድሬሽን የሲሸልስ ብሄራዊ ቢድን ከኢትዮጵያ አቻው ጋር ላለበት ጋቦን ለምታዘጋጀው የ2017 የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ አዲስ አሰልጣኝ መሾሙን ተቀማጭነቱን በሲሸልስ ያደረገው ቱደይ ስፓርት ዘግቧል፡፡ እግርኳስ ፌድሬሽኑ የላ ፓስ ክለብ አሰልጣኝ የሆኑትን ብሩኖ ሳኢንዲኒን በግዜያዊነት አሰልጣኝነት ቀጥሯል፡፡ አሰልጣኝ ሳኢንዲኒ የሲሸልስ ክለብ የሆነውን የላ ፓስ ክለብ አሰልጣኝ ሲሆኑ የዚሁ ክለብ ታዋቂ የአጥቂ መስመር ተጫዋች ነበሩ፡፡ ሮድኒ ኮዚ የሳኢንዲኒ ምክትል ሆነው ይሰራሉ፡፡ የሲሸልስ እግርኳስ ፌድሬሽን ስለቅጥሩ ሁኔታ የሰጠው መግለጫ የለም፡፡
አዲሱ አሰልጣኝ ብሩኖ ሳኢንዲን ለቱደይ ስፓርት በሰጡት አስተያየት ብሄራዊ ብድኑን በተሰጣቸው አጭር ግዜ እንደሚያዘጋጁ ተናግረዋል፡፡ “ባሉን ጥቂት ቀናት ብድኑን ለጨዋታው እናዘጋጃለን፡፡ ነገር ግን ጨዋታው በጣም ከባድ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ የተቻለንን አድርገን ውጤት ለማምጣት እንጥራለን፡፡” ብለዋል አሰልጣኙ፡፡
አሰልጣኝ ሳኢንዲኒ የቀድሞ የሲሸልስ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ የሆኑትን ኡሪክ ማቲኦትን ተክተዋል፡፡ ማቲኦት ሪዮኒየን ደሴት ባዘጋጀችው የህንድ ውቅያኖስ ደሴቶች ጨዋታ ውድድር በኃላ ውላቸው በማለቁ ከብድኑ ተለይተዋል፡፡ ብሄራዊ ብድኑ በቻን 2016 ማጣሪያ በሞዛምቢክ ውጪ መሆኑ እንዲሁም በህንድ ውቅያኖስ ደሴቶች ጨዋታ ውድድር ከምድቡ በግዜ መሰናበቱ የማቲኦትን መሰናበትን አፋጥኖታል፡፡
አሰልጣኝ ሳኢንዲኒ አዳዳሲ ተጫዋቾች ለኢትዮጵያ ው ግጥሚያ ጠርተዋል፡፡ ሲሸልስ በመጀመሪያው ጨዋታ በአልጄሪያ 4-0 ተሸንፋለች፡፡ ሲሸልስ በመጪው ቅዳሜ በዩኒቲ ስታዲየም ኢትዮጵያን ታስተናግዳለች፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *