መብራት ኃይል አሰልጣኙ ዮርዳን ስቶይኮቭን አሰናበተ


መብራት ኃይል ላለፉት 4 የውድድር ዘመናት ቡድኑን ያሰለጠኑት ዮርዳን ስቶይኮቭን ማሰናበቱን ፕላኔት ስፖርት ዘግቧል፡፡

በ2003 ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ዮርዳን 4 የውድድር ዘመናትን በቀዮቹ ቤት ያሳለፉ ሲሆን በ2004 የውድድር ዘመን 3ኛ የወጣውን አምና ደግሞ ላለመውረድ የጠፋለመውን ቡድን የመሩትን አሰልጣኝ ኮንትራት ለቀጣዮቹ 2 አመታት እንዳራዘመ ሲነገር የቆየ ቢሆንም ማን እንዳስፈረማቸው የተረጋገጠ ነገር የለም፡፡

መብራት ኃይል ለአሰልጣኙ ስንብት ምክንያት ያደረገው የሚከፈላቸው ከፍተኛ ደሞዝ እና እያስመዘገቡት ያለው ውጤት አለመመጣጠን እንደሆነ ተገምቷል፡፡

ባለፈው ሰኞ የቀጣዩን የውድድር ዘመን ዝግጅት በሀዋሳ የጀመሩት መብራት ኃይሎች በምክትሎቹ አጥናፉ አለሙ እና ብርሃኑ ባዩ በጊዜያዊነት ይመራል፡፡

ምንጭ – ፕላኔት ስፖርት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *