በቤልጅየም ዝቅተኛ ዲቪዝዮን ክለቦች ውስጥ የሚጫወቱት ወንድማማቾቹ ካሌብ ሁንዱራ እና ናኦድ ሁንዱራ አንድ ቀን ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የመጫወት ህልም አላቸው፡፡
ታላቅየው ካሌብ የ22 አመት ወጣት ሲሆን በቤልጅየም አምስተኛ ዲቪዝዮን ለሚገኘው ኬ.ኤፍ.ሲ ሩምቤኬ ይጫወታል፡፡ የ21 አመቱ ናኦድ ሁንዴራ ደግሞ በ3ኛ ዲቪዝዮን ለሚገኘው ኢዚገም ክለብ ይጫወታል፡፡
ሁለቱ ተጫዋቾች ከዚህ ቀደም በ2010 ከፍ ያለ ደረጃ የመድረስ እድል አጋጥሟቸው ነበር፡፡ ታላቅየው ካሌብ በኖርዊት ሲቲ ታናሹ ናኦድ ደግሞ በአርሰናል የሙከራ ጊዜ አሳልፈውም ነበር፡፡
የሁለቱ ተጫዋቾች አባት የሆኑት አቶ ሁንዱራ ከአመት በፊት በሙኒክ በተካሄደው የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌስቲቫል ላይ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻውን አግኝተው ስለ ልጆቻቸው ማስረዳታቸውን ገልፀው ከአሰልጣኙ ጋር መልካም ውይይት እንዳደረጉ ተናግረዋል፡፡
እንደ አባታቸው ሁሉ ሁለቱም ተጫዋቾች አንድ ቀን ለዋልያዎቹ የመጫወት ምኞት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡
ወንድማማቾቹ ተጫዋቾች ከዚህ ቀደም በሶከር ኢትዮጵያ ላይ ካስተዋወቅናችሁ አላዛር ዘርአብሩክ ጋር የስጋ ዝምድና አላቸው፡፡ (የ14 አመቱ አላዛር በአርሰናል የሙከራ ጊዜ በማሳለፍ ላይ ይገኛል፡፡
Photo – left to right —> Kaleb Hundura, Naod Hundura, Kaleb and Naod With Alazar Zerabiruk
Bottom – Kaleb and Naod with their Mother