የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ላለፉት ሁለት አመታት በዋልያዎቹ ዋና ስፖንሰርነት የቆየው ሄይኒከን ኢትዮጵያን የስፖንሰር ሺፕ ውል ማራዘሙን የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ጁነይዲ ባሻ በትዊተር ገፃቸው አረጋግጠዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄረዊ ቡድን በ2005 ዓ.ም ለ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉን ተከትሎ ከሄይኒከን ጋር ለ2 አመታት የ24 ሚልዮን ብር የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት መስማማቱ የሚታወስ ሲሆን በቀጣይ ለስንት አመታት ከዋልያዎቹ ጋር በአጋርነት እንደሚቆይና የስምምነት ዋጋው ምን ያህል እንደሆነ ያሉት ነገር የለም
ፌድሬሽኑ ከዚህ በተጨማሪ ከቲቪ 5 ጋር 60 ሺህ ዶላር ዋጋ ያለው ስምምነት መፈራረማቸውንና በቅርቡ ፌዴሬሽኑን በገቢ ለማጠናከር ቴሌቶን እንደሚዘጋጅ ተናግረዋል፡፡ ፌዴሬሽኑ ከቴሌቶኑ 20 ሚልዮን ብር ገደማ ይሰበስባል ተብሎ ይጠብቃል፡፡