የክረምት ወሬዎች


መብራት ኃይል ሰኞ እለት 28 ተጫዋቾችን ይዘው ወደ ሀዋሳ ለዝግጅት ሄዷል፡፡ ቀዮቹ ከዋናው ቡድን 22 ፣ አዲስ ዩጋንዳዊ ተጫዋች እና ከሁለተኛው ቡድን ያደጉ 5 ተጫዋቾችን በቡድናቸው አካተዋል፡፡

የቢያድግልኝ ኤልያስ የደቡብ አፍሪካ የሙከራ ቆይታ ሳይሳካ እንዳልቀረ ተነግሯል፡፡ ተጫዋቹ ሙከራውን እያሳለፈበት ያለው ክለብ ይፋ ባይሆንም አስፈላጊ የዝውውር ጉዳዮችን አጠናቆ ለቪዛ ጉዳዮች ወደ ኢትዮጵያ መመለሱ ተወርቷል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ውሉን ያራዘመው ዘሪሁን ታደለ የተከፈለው ገንዘብ የኢትዮጵያ የግብ ጠባቂዎች የፊርማ ክፍያ ከርድን እንደሰበረ ተወርቷል፡፡ ዘሪሁን ለማራዘምያው 900 ሺህ ብር እንደተቀበለ ሲነገር ከዚህ ቀደም በሲሳይ ባንጫ የተያዘውን ሪኮርድ ሰብሯል ተብሏል፡፡ በተያያዘ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለፋሲካ አስፋው ፊርማ እስከ 1.1 ሚልዮን ብር መክፈሉ ተሰምቷል፡፡

ባለፈው አመት ደደቢትን የተቀላቀለው ሚካኤል ጆርጅ ቀሪ የአንድ አመት ውሉን 300 ሺህ በመክፈል አቋርጦ ወደ ዳሽን ቢራ አቅንቷል፡፡ ሚካኤል ለፊርማ ከዳሽን 750 ሺህ ብር ተከፍሎታል፡፡

ያሬድ ዝናቡ ደደቢትን መቀላቀሉ እርግጥ ሆኗል፡፡ ሁለገቡ የቀድሞ የአዳማ ከነማ አምበል ያሬድ ከሰማያዊው ጦር ለፊርማ 900 ሺህ ብር ተከፍሎታል፡፡

ደደቢት ወጣቱ አማካይ ሄኖክ ኢሳያስን በውሰት ወደ ዳሽን ቢራ ልኮታል፡፡ አምና በበርካታ ጨዋታዎች ላይ የተሰለፈው ሄኖክ አዲሱን የውድድር ዘመን በጎንደር ያሳልፋል፡፡

ውብሸት ደሳለኝ የኢትዮጵያ ቡና የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ሆኖ መሾሙ ተነግሯል፡፡ የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ መድን እና መከላከያ ግብ ጠባቂ ባለፈው የውድድር ዘመን ከተጫዋችነት አለም የተገለለ ሲሆን የአብዱሳላህ ፈቱሼን ቦታ ተክቶ ይሰራል፡፡

ተስፈኛው ዳዋ ኢቲሳ የቅዱስ ጊዮርጊስ ንብረት ሳይሆን እንዳልቀረ ተወርቷል፡፡ የናሽናል ሲሚንቶው አማካይ ከዋልያዎቹ ጋር ለዝግጅት በብራዚል የሚገኝ ሲሆን ከብራዚል መልስ ለፈረሰኞቹ ይፈርማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

.

.

.

ምንጭ – ፕላኔት ስፖርት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *