ጅማ አባ ጅፋር ሁለት ተጫዋቾች አስፈርሟል

ትላንት የ5 ተጫዋቾችን ፊርማ ያገኘው ጅማ አባ ጅፋር ዛሬ ደግሞ ሁለት ተጫዋቾችን ማስፈረሙን አስታውቋል።

አክሊሉ ዋለልኝ ወደ ጅማ አባ ጅፋር ያመራ ተጫዋች ነው። በኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ቡድን ያሳየውን ብቃት ተከትሎ ከሀዋሳ ወደ ኢትዮጵያ ቡና በማምራት ያለፉት ሦስት የውድድር ዘመናት የቆየው አክሊሉ በቡና ውላቸው ተጠናቆ ከተለያዩ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የነበረ ሲሆን በሁለት ዓመት ውል ወደ ጅማ ማምራት ችሏል።

ሲሳይ ቶሊ አዳማን ለቆ ወደ ጅማ አምርቷል። በ2008 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ለቆ ወደ አዳማ ያመራው ሲሳይ ውሉን አጠናቆ ወደ አባ ጅፋር በሁለት ዓመት ኮንትራት ያመራ ሲሆን በግራ ተከላካይ እና አማካይ ሆኖ መጫወት ይችላል።