ሀላባ ከተማ የወሳኝ የግብ ዘቡን ውል አራዝሟል

ሀላባ ከተማ የወሳኝ የግብ ዘቡን ውል አራዝሟል

አዲስ አዳጊዎቹ ቡድናቸውን ማጠናከር ተያይዘውታ።

ከዚህ ቀደም የነባር ተጫዋቾችን ውል አራዝመው ኮንኮኒ ሀፍዝ ፣ ካሌብ አማንክዋህ እና ሴኔጋላዊ የተከላካይ አማካይ ሳምባ ሴክ ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት አዲስ አዳጊዎቹ ሀላባ ከተማዎች አሁን ደግሞ የወሳኝ ግብ ጠባቂያቸውን አባቱ ጃርሶን ውል ማራዘማቸው ታውቋል።

ከሸገር ከተማ ቡድኑን ተቀላቅሎ ያለፈውን አንድ ዓመት ከበድኑ ጋር የቆየው ግብ ጠባቂው ሀላባ ወደ ሊጉ እንዲያድግ ትልቁን ሚና ከተወጡ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው።