ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ወሳኝ አጥቂያቸውን አቆይተዋል

ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ወሳኝ አጥቂያቸውን አቆይተዋል

ያለፉትን ሦስት ዓመታት ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ድንቅ ብቃቱን ሲያስመለክተን የቆየው አጥቂ ውሉን አራዝሟል።

ከጅማ ምድር ተገኝቶ በክለብ ደረጃ በባቱ ከተማ፣ በጅማ አባ ጅፋር ፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ(በከፍተኛ ሊግ ቡድኑን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ በማሳደግ)፣ በኢትዮ ኤሌክትሪክ በሁለት አጋጣሚዎች ወደ ፕሪሚየር ሊጉ በማሳደግ የሚታወቀው እና ያለፉትን ሦስት ተከታታይ ዓመት የቡድኑ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን የሚያጠናቅቀው አቤል ሐብታሙ ለተጨማሪ ዓመት ለመቆየት መስማማቱን ሰምተናል።

በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የሚመሩት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች እስካሁን የፍራኦል መንግስቱ ፣ አማኑኤል ግዛቸው እና የእሱባለው ሙሉጌታን ዝውውር ያጠናቀቁ ሲሆን አሁን ደግሞ የወሳኝ አጥቂያቸውን ውል ማራዘማቸው ለቡድኑ እፎይታ የሚሰጥ ሆኗል።