የ2007 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፕሮግራም ይፋ ሆነ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የ2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፕሮግራምን ይፋ አድርጓል፡፡ዘኪህ ቀደም ሊጀመር ሳምንት ሲቀረው ይወጣ የነበረው ፕሮግራም ዘንድሮ ባልተለመደ ሁኔታ ቀደም ብሎ ወጥቷል፡፡

የሚጀመርበት ቀን ያልተገለፀው የፕሪሚየር ሊጉ ፕሮግራም ቻምፒዮኖቹን ከብሄራዊ ሊግ ካደጉ ክለቦች ጋር ያገናኛል፡፡ የአምናው የፕሪሚየር ሊግ ቻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አዳማ ተጉዞ የብሄራዊ ሊግ ቻምፒዮኑ አዳማ ከነማን ሲገጥም የጥሎ ማለፍ አሸናፊው ደደቢት በበኩሉ ሌላውን አዲስ መጪ ወልዲያ ከነማን ይገጥማል፡፡

ክረምቱን በምርጥ ግዢዎች ያሳለፈው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮጵያ ቡናን ሲገጥም መከላከያ መብራት ኃይልን በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ስታድየም ይገጥማሉ፡፡ የስታድየም ስራውን እያገባደደ ያለው ወላይታ ድቻ ዳሽን ቢራን በሶዶ ሲገጥም ፣ ይርጋለም ላይ ሲዳማ ቡና ሙገር ሲሚንቶን ፣ ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከነማ አርባምንጭ ከነማን ያስተናግዳሉ፡፡

የአንደኛው ሳምንት መርሃ ግብር ይህንን ይመስላል

ደደቢት ከ ወልዲያ ከነማ — አዲስ አበባ

አዳማ ከነማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ — አዳማ

ሲዳማ ቡና ከ ሙገር ሲሚንቶ — ይርጋለም

ሀዋሳ ከነማ ከ አርባምንጭ ከነማ — ሀዋሳ

ኢትዮጵያ ቡና ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ — አዲስ አበባ

ወላይታ ድቻ ከ ዳሽን ቢራ — ሶዶ

መከላከያ ከ መብራት ኃይል —አዲስ አበባ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *