ዋልያዎቹ የብራዚል ቆይታቸውን በአቻ ውጤት አጠናቀቁ

ላለፉት 3 ሳምንታት በብራዚል ከትሞ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ትላንት ምሽት ባደረገው የመጨረሻ ጨዋታ ከአናፖሊና ክለብ ጋር አቻ በመለያየት አጠናቋል፡፡

በጨዋው ግብ በማስቆጠር ቅድሚያውን የያዘው የብራዚሉ ክለብ ሲሆን ሽመልስ በቀለ ዋልያዎቹን አቻ አድርጎ የመጀመርያው አጋማሽ ተጠናቋል፡፡

ከእረፍት መልስ አናፖሊና በድጋሚ ግብ አስቆጥረው መምራት ሲችሉ የመስመር ተከላካዩ አበባው ቡታቖ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአቻነት ግብን አስቆጥሯል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በብራዚል በቆየባቸው 21 ቀናት 5 የወዳጅነት ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን በሶስቱ ተሸንፎ በ2 አቻ ወጥቶ ካለምንም ድል ወደ ሃገር ቤት ይመለሳል፡፡

Photo – Yosef Tesfaye

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *