ለድሬዳዋ ከነማ ትላንት ከፍተኛ ሽልማት ተበርክቷል

የብሄራዊ ሊግ ቻምፒዮን ሆኖ ፕሪሚየር ሊጉን የተቀላቀለው ድሬዳዋ ከነማ እግርኳስ ክለብ ትላንት ከከተማ መስተዳድሩ የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡

ትላንት ምሽት በድሬዳዋ ራስ ሆቴል በተደረገው የሽልማት ስነስርአት የከተማ መስተዳድሩ ከንቲባ አቶ ሃሰን ዚያድ እና ሌሎች የስራ አመራሮች እንዲሁም የድሬዳዋ ከነማ አሰልጣኞች እ ተጫዋቾች ተገኝተዋል፡፡

የከተማ መስተዳድሩ ለቡድኑ አባላት እንዳበረከቱት አስተዋፅኦ ደረጃ ወጥቶላቸው የሚከፋፈል 3 ሚልዮን ብር ሽልማት ያበረከተ ሲሆን የቢጂአይ ኢትዮጵያ የምስራቅ ዲስትሪክት 150 ሺሀ ብር ሽልማት አበርክቷል፡፡

የድሬዳዋ ስፖርት ኮሚሽን ለአሰልጣኝ መሰረት ማኒ የወርቅ ሃብል በስጦታ ሲያበረክት የከተማው የሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ የላፕቶፕ ሽልማት አበርክቷል፡፡

የከተማ መስተዳድሩ ከንቲባ አቶ ሀሰን ዚያድ ባደረጉት ንግግር ውጤቱ የሚያኩራራ ሳይሆን ለበለጠ ስራ የሚነሳሳ እንደሆነ ተናግረው አስተማማኝ ውጤት ለማምጣት በመሰረተ ህዝብ ስራዎች ላይ እደሚሰሩና ክለቡም ለታዳጊዎች ትኩረት መስጠት እዳለበት አሳስበዋል፡፡ ክለቡ የሚጓጓዝበት ዘመናዊ አውቶብስ በቅርቡ እንደሚበረከትለትና በፕሪሚየር ሊጉ ውጤታማ ከሆኑም ከፍተኛ ሽልማት እንደሚጠብቃቸው ቃል ገብተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለጨዋታ ድሬዳዋ ለሚመጡ ቡድኖች የሚገለግል አምቡላንስ እንደሚገዛ ተናግረዋል፡፡

የድሬዳዋ ከነማ እግርኳስ ክለብ ህዝብ ግንኙነት አቶ ጌቱ ተገኝ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደተናገሩት የክለቡ ተጫዋቾች እና የአሰልጣኝ ቡድኑ በተበረከተላቸው ሽልማት ደስተኞች ናቸው፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *