የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን መስከረም 19 ከቦትስዋና ጋር በጋቦሮኒ ለሚያደርገው የአቋም መለኪያ ጨዋታ ፣ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ለሚያደርገው የአለም ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ እንዲሁም ከቡሩንዲ ጋር ለሚደርገው የቻን ማጣሪያ ዝግጅት 19 ተጫዋቾች ተመርጠዋል፡፡
ፌዴሬሽኑ ሁሉም ተጫዋቾች መስከረም 10 ሪፖርት በማድረግ ሆቴል መሰባሰብ እንደሚጠበቅባቸው ያሳሰበ ሲሆን ተጨማሪ ተጨዋቾች ከ2007 የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች በኋላ እንደሚለዩ የብሄራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ አስታውቀዋል፡፡
ግብ ጠባቂዎች
ታሪክ ጌትነት ፣ ለአለም ብርሃኑ እና አቤል ማሞ
ተከላካዮች
ስዩም ተስፋዬ ፣ ተካልኝ ደጀኔ ፣ አሰቻለው ታመነ ፣ አንተነህ ተስፋዬ ፣ ሙጂብ ቃሲም እና ዘካርያስ ቱጂ
አማካዮች
ኤፍሬም አሻሞ ፣ ጋቶች ፓኖም ፣ ሙሉ ዓለም መስፍን ፣ ብሩክ ቃልቦሬ ፣ ቢኒያም በላይ ፣ በረከት ይስሃቅ እና አሰቻለው ግርማ
አጥቂዎች
ባዬ ገዛሀኝ ፣ ዳዊት ፈቃዱ እና ራምኬል ሎክ
(c) EFF