የከፍተኛ ሊግ አጫጭር መረጃዎች 

ወልቂጤ አሰልጣኝ ቀጥሯል

የምድብ ለ ተሳታፊው ወልቂጤ ከተማ አዲሴ ካሳን ወደ ሀዋሳ ከተማ ከሸኘ በኋላ አዲስ አሰልጣኝ ሲያፈላልግ ቆይቶ ደረጄ በላይን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ቀጥሯል። በ2008 ጅማ አባ ቡናን ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ያስቻሉት አሰልጣኝ ግርማ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ኢትዮጵያ መድንን ተረክበው እስከ አጋማሽ ከቆዩ በኋላ መለያየታቸው ይታወሳል። ከመስከረም 2011 ጀምሮ ቡድኑን የሚረከቡት አሰልጣኝ ደረጄ የአንድ ዓመት ውል መፈራረማቸውን እና የክለቡን የመጨረሻ ጨዋታዎች እየተመለከቱ እንደሆነ ለሶከር ኢትዮጵያ ገለፀዋል።

አክሱም ከተማ ጌታቸው ዳዊትን አስቀጥሏል

አክሱም ከተማን ከዓመቱ አጋማሽ ጀምረው በመረከብ የተሻሻለ ቡድን ያሳዩት አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊትን ለአንድ ዓመት ውላቸውን እንዳራዘመ የክለቡ ስራ አስኪያጅ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጸዋል። በተያየዘም አክሱም ከተማ የ2011 የውድድር ዘመን ዝግጅቱን በቅርቡ እንደሚጀምር እና ለመጪው የውድድር ጊዜ ጥሩ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ እየሰራ እንደሆነ  ጨምረው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ መድን

የኢትዮጵያ መድን የከፍተኛ ሊግ ውድድር በተጠናቀቀ ማግስት ለ2011 ቅድመ ዝግጅቱን መጀመሩ ታውቋል። ክለቡ በቢሾፍቱ ወጣት ተጫዋቾችን በመመልመል ላይ ሲገኝ ዋና አሰልጣኝ ቅጥር በቅርቡ ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። ሶከር ኢትዮጵያ ባገኘው መረጃ ሌ

ልምድ ያላቸውን ጨምሮ ከ29 በላይ አሰልጣኞች ለቀድሞው ተወዳጅ ክለብ ስራ ተመዝግበዋል። ለሶስት ጊዜያት ከፕሪምየር ሊግ በመውረድ ከቀዳሚዎቹ ተርታ የሚመደበው መድን በ2006 ከወረደ ወዲህ ወደ ፕሪምየር ሊግ አልተመለሰም።

ተስተካካይ ጨዋታ 

በዛሬው እለት ድሬዳዋ ፖሊስ በአካባቢው በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ሳያከናውነው የቀረው የ27ኛ ሳምንት ተሰነካካይ መርሐ ግብርን ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር አከናውኖ 1-1 በመለያየት ከወራጅ ቀጠናው የመውጣት እድሉን አምክኗል።

የደረጃ ሰንጠረዥ


ቅሬታዎች

ዓመቱን ሙሉ የክለቦች ቅሬታን ሲያስተናግድ የቆየው ከፍተኛ ሊጉ ወደ መገባደጃው ቢቃረብም የተስተካካይ ጨዋታዎች እና የክስ ጉዳዮች በቶሎ እልባት አለማግኘት ለተጨማሪ ቅሬታ በር ከፍቷል። በምድብ ለ የ30ኛው ሳምንትን ጨምሮ በርካታ ተስተካካይ ጨዋታዎች የሚቀሩ ከመሆናቸው ባሻገር መቼ እንደሚደረጉ በፍጥነት አለመታወቁ ከበጀት መጨረስ ጋር ተደማምሮ ፈታኝ ጊዜ እያሳለፉ እንደሆነ ክለቦች ለሶከር ኢትዮጵያ እየገለፁ ይገኛሉ።

በምድብ ሀ ጨዋታዎች ሙሉ ለሙሉ ቢጠናቀቁም የወራጅ ቀጠናው ውዝግብ አሁንም ቀጥሏል። በሽረው ጨዋታ የሁለት ተጫዋቾች የተግቢነት ክስ ያሳያዙት ፌዴራል ፖሊሶች በአፋጣኝ መልስ እንዲሰጣቸው በደብዳቤ ቢጠይቁም እሳካሁን ምላሽ እንዳልተሰጠ እና ጉዳዩን በማጣራት ላይ እንዳሆነ ተገልጿል።

ቀጣይ የምድብ ለ መርሐ ግብር

ሰኞ ነሀሴ 21 ቀን 2010

ደቡብ ፖሊስ ከ ድሬዳዋ ፖሊስ (30)

ወልቂጤ ከተማ ከ ሀላባ ከተማ (30)

ሀዲያ ሆሳዕና ከ ጅማ አባቡና (30)

ቡታጅራ ከተማ ከ ካፋ ቡና (30)

ቅዳሜ ነሀሴ 26 ቀን 2010

ቤንች ማጂ ቡና ከ ናሽናል ሴሜንት (30)

ረቡዕ ነሀሴ 30 ቀን 2010

ሻሸመኔ ከተማ ከ ስልጤ ወራቤ (30)

መቂ ከተማ ከ ሀምበሪቾ (30)

ዲላ ከተማ ከ ነጌሌ ከተማ (30)

ቤንች ማጂ ቡና ከ ድሬዳዋ ፖሊስ (28)

ቀን ያልተቆረጠላቸው ጨዋታዎች

ናሽናል ሴሜንት ከ ቡታጅራ ከተማ (27)

ወልቂጤ ከተማ ከ ካፋ ቡና (ተቋርጦ ያላለቀ)