አብርሀም መብራቱ የብሔራዊ ቡድን ስብስባቸውን ወደ 23 ቀንሰዋል

ከነሀሴ 2 ጀምሮ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት ከተጠሩት ተጫዋቾች መካከል 9 ተጫዋቾችን ቀንሷል። 

አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ በአቋም እና ጉዳት ምክንያት የቀነሷቸው ዘጠኝ ተጫዋቾች ተመስገን ካስትሮ፣ በዛብህ መለዮ፣ ዐወት ገ/ሚካኤል፣ እስራኤል እሸቱ፣ አቤል ማሞ፣ አዲሱ ተስፋዬ፣ አማኑኤል ገ/ሚካኤል፣ ሰለሞን ሀብቴ እና ታፈሰ ሰለሞን ናቸው።

ብሔራዊ ቡድኑ ዘጠኝ ተጫዋቾችን መቀነሱን ተከትሎ ነገ እና ከነገ በስቲያ ተጠቃለው ከውጪ ሀገር ክለቦች ከሚመጡ ተጫዋቾች ጋር ተደምሮ 23 ተጫዋቾችን የያዘ ሲሆን እሁድ በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታድየም ሴራሊዮንን እስከሚገጥምበት ጨዋታ ድረስ ልምምዱን የሚቀጥል ይሆናል። 

ቀሪው የዋልያዎቹ ስብስብ 

ግብ ጠባቂዎች (3)

ሳምሶን አሰፋ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ተክለማርያም ሻንቆ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ጽዮን መርዕድ (አርባምንጭ ከተማ)

ተከላካዮች (8)

ሳልሀዲን ባርጌቾ (ቅ/ጊዮርጊስ)፣ አስቻለው ታመነ (ቅ/ጊዮርጊስ)፣ ሙጂብ ቃሲም (ፋሲል ከነማ)፣ አንተነህ ተስፋዬ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ አብዱልከሪም መሀመድ (ቅ/ጊዮርጊስ)፣ ኄኖክ አዱኛ  (ቅ/ጊዮርጊስ)፣ አምሳሉ ጥላሁን (ፋሲል ከተማ)፣ አህመድ ረሺድ (ኢትዮጵያ ቡና)

አማካዮች (6)

ጋቶች ፓኖም (ኤል ጎውና)፣ ሙሉአለም መስፍን (ቅ/ጊዮርጊስ)፣ ናትናኤል ዘለቀ (ቅ/ጊዮርጊስ)፣ አማኑኤል ዮሀንስ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ቢኒያም በላይ (ስከንደርቡ ኮርሲ)፣ ሽመልስ በቀለ (ፔትሮጀት)

አጥቂዎች (6)

አዲስ ግደይ (ሲዳማ ቡና)፣ አቤል ያለው (ቅ/ጊዮርጊስ)፣ ዑመድ ኡኩሪ (ስሞሀ)፣ በኃይሉ አሰፋ (ቅ/ጊዮርጊስ)፣ ጌታነህ ከበደ (ቅ/ጊዮርጊስ)፣ ዳዋ ሁቴሳ (አዳማ ከተማ)