የዋልያዎቹ ጋዜጣዊ መግለጫ ……

ዋልያዎቹ ትላንት አመሻሽ ላይ በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ መግለጫውን የሰጡት የብሄራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ እና ተጫዋቾቹ ብርሃኑ ቦጋለ ፣ ጀማል ጣሰው እና አዳነ ግርማ ናቸው፡፡ በመግለጫው ወቅታዊ የብሄራዊ ቡድኑ ሁኔታ የተነሳ ሲሆን ፣ ስለ መገናኛ ብዙሃን እና የብራዚል ቆይታ ብዙ ተብሏል፡፡

ተጫዋቾቹ እና አሰልጣኙ በመግለጫው ከተናገሯቸው አንኳር አንኳሩን መርጠን አቅርበንላችኋል፡፡

ማርያኖ ባሬቶ

— ‹‹ ብራዚል የሄድነው ለጠንካራ ዝግጅት እንጂ ለመዝናናት አይደለም፡፡ ከዚህ ቀደም ተጨዋቾቹን የማላውቃቸው በመሆኑ ያደረግናቸው የዝግጅት ጨዋታዎች የተጫዋቾቼን ብቃት ለመረዳት ጠቅመቀውኛል፡፡ ››

—- ‹‹ ከ20 አመት በታች ቡድን በመጡት ተጫዋቾች (አንዳርጋቸው ይላቅ ፣ ዳዋ ኢቲሳ እና ናትናኤል ዘለቀ) ተደንቄያለሁ፡፡ ትዛዝ ለመቀበል እና ለመተግበር ሁልጊዜ ዝግጁ በመሆናቸው በቀላሉ ተግባብተናል፡፡ ››

—- ‹‹ ድክመታችንን ለመቅረፍ እየሰራን ነው፡፡ በራሳችን ሜዳ ለረጅም ሰአት ኳስን ማቆት ፣ የግብ እድል የመፍጠር ችግር እና የመስመር አጨዋወታችንን ለማሻሻል እየሰራን ነው፡፡ ››

—- መላው ኢትዮጵያዊ ከጎናችን እንዲቆም እንፈልጋለን፡፡ ጊዜ ሊሰጠንና ድጋፍ ሊያደርግልን ይገባል፡፡ እኔ የውጭ ዜጋ ብሆንም ቡድኑ የእናንተ ነው ››

— ‹‹ በአልጄርያው ጨዋታ የማጥቃት ባህርይ ያለቸው ተጫዋቾችን አብዝቼ እጠቀማለሁ፡፡ አጥቅተን እንጫወታለን ››

አዳነ ግርማ

—- ‹‹ አሰልጣኙ ስለ እኛ ምንም ግንዛቤ አልነበራቸውም፡፡ የብራዚሉ ዝግጅት አቋማችንን ለመለየት ጠቅሟቸዋል፡፡ ለእኛም መልካም ልምድ አግኝተንበታል፡፡ ››

—- ‹‹የመገናኛ ብዙሃኑ በቡድኑ ላይ የሚሰነዝረው ትችት ፍትሃዊ አይደለም፡፡ የወዳጅነት ጨዋታ ሲጠፋ ለምን ይጠፋል ፤ ሲገኝ ደግሞ ለምን ከደካማ ቡድን ጋር ሆነ የሚለው ትችት አግባብ አይደለም፡፡ ››

ጀማል ጣሰው

—– ‹‹ የብራዚሉ የዝግጅት ጊዜ አሁን ያለንበትን ደረጃ እንድናውቅ ጠቅሞናል፡፡ ››

ብርሃኑ ቦጋለ

—– ‹‹ የብራዚል ቆይታችን መልካም ነበር፡፡ ከአልጄርያ ጋር የምናደርገው ጨዋታ በሜዳችን እንደመሆኑ የሜዳ አድቫንቴጅ መጠቀም ይኖርብናል፡፡ ››

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *