ብርሃኑ ቦጋለ የብሄራዊ ቡድኑ አምበል ሆኖ ተመረጠ

ማርያኖ ባሬቶ የደደቢቱን የግራ መስመር ተከላካይ እና አምበል ብርሃኑ ቦጋለ ‹‹ ፋዲጋ ››ን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አምበል አድርገው ሾመውታል፡፡

ብሄራዊ ቡድኑ ከቻን በ ጊዜ ከምድቡ መሰናበቱን ተከትሎ የዋልያዎቹ ዋና እና 3ኛ አምበል የነበሩት ደጉ ደበበ እና አይናለም ኃይለ ከብሄራዊ ቡድኑ ራሳቸውን ማግለላቸው የሚታወስ ሲሆን ከዛ ወዲህ በተደረጉ የወዳጅነት ጨዋታዎች ባሬቶ የተለያዩ ተጫዋቾችን አምበል አድርገው ሲያጫውቱ ቆይተዋል፡፡

ባለፉት 3 አመታት ከደጉ ደበበ ቀጥሎ ምክትል አምበል የነበረው አዳነ ግርማ እና በብራዚል የዝግጅት ጨዋታዎች አምበል የነበረው አበባው ቡታቆ ለአምበልነቱ ሰፊውን ግምት ቢያገኙም አሰልጣኙ ብሄራዊ ቡድኑ ብዙም የቋሚ ተሰላፊነት እድል የማያገኘው ባርሃኑ ቦጋለን መምረጣቸው አስገራሚ ሆኗል፡፡

ብርሃኑን ተከትሎ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ኢትዮጵያ ቡናን ለቆ መከላከያን የተቀላቀለው ግብ ጠባቂው ጀማል ጣሰው 2ኛ አምበል ሆኖ ተሹሟል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *