ኢትዮጵያ ቡና ለማስፈረም ከስምምነት ደርሶ የነበረው ኮንጓዊው አጥቂ ሱሌይማን ሎክዋን አስፈርሟል።
የአጥቂ መስመር ተጫዋቹ ባለፈው የውድድር ዓመት መጨረሻ ከዛምቢያው ክለበ ናፕሳ ስታርስ ጋር ከተለያየ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከ20 ቀናት በላይ በኢትዮጵያ ቡና የሙከራ ጊዜ ያሳለፈ ሲሆን ክለቡን ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሶ የነበረ ቢሆንም የመኖርያ ፈቃድ እና ተያያዥ ጉዳዮችን ሲያጠናቅቅ ቆይቶ በመጨረሻም በሁለት ዓመት ውል የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች መሆኑ ተረጋግጧል።
የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ዜግነት ያለው የቀድሞ የዛናኮ አጥቂ በኢትዮጵያ ቡና ከዩጋንዳዊኖቹ ክሪዚስቶም ንታምቢ እና ኢስማኤል ዋቴንጋ እንዲሁም ከጋናዊው አልሀሰን ካሉሻ አራተኛው የውጪ ዜጋ ሆኗል።