ወልዋሎ በሦስት ተጫዋቾቹ ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ የዲሲፕሊን ኪሚቴ ውድቅ አደረገው

በ2010 የውድድር ዘመን ወልዋሎን ሲያገለግሉ የነበሩት ወግደረስ ታዬ ፣ መኩርያ ደሱ ፣ ከድር ሳህሊ እና አታክልቲ ፀጋዬ ክለቡ በቅድመ ውድድር ዝግጅት ነሐሴ 19 ወደ ካምፕ እንዲገቡ የሰጠሁትን ትዕዛዝ ሌሎች የቡድኑ ተጫዋቾች ጥሪውን አክብረው ሲገኙ እነርሱ ግን በተደጋጋሚ ጥሪ ቢደረግላቸውም ሊገቡ አልቻሉም ። ሆኖም ከድር ሳሊህ እና አታክልቲ ፀጋዬ ጋር ጉዳዩ በስምምነት ሲቋጭ በተለይ ወግደረስ ታዬ እና መኩርያ ደሱ ሊገቡ ባለመቻላቸው በክለቡ የዲሲፒሊን ደንብ መሰረት አሰናብተዋቸው እንደነበረ ይታወቃል ።

ተጫዋች ከድር ሳሊህ ከክለቡ ጋር በስምምነት መለያየቱን ተከትሎ ወደ አዲስ አበባ ከተማ እንደተዘዋወረ ሲታወቅ ሦስቱ ተጫዋቾች (ወግደረስ ታዬ ፣ መኩርያ ደሱ እና አታክልቲ ፀጋዬ) የወልዋሎ እግርኳስ ክለብ የወሰነብን ውሳኔ ተገቢ አይደለም ክለቡ ወደ ዝግጅት እንድንገባ ያስተላለፈልን ጥሪ የለም በሚል ለፌዴሬሽኑ ዲሲፕ.ሊን ኮሚቴ አቤቱታቸውን በደብዳቤ አሳውቀዋል።

ጉዳዩን በዝርዝር ሲከታተል የቆየው የዲሲፒየፕሊን ኮሚቴ የሚመለከታቸውን ሁለቱን አካላት ስለ ጉዳዮ በደብዳቤ ማብራርያ እንዲሰጡ በማድረግ ከመረመረ በኋላ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል።

*የወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ ስፖርት ክለብ በተጫዋቾቹ ላይ ከክለቡ እንዲሰናበቱ የወሰነው ውሳኔ ተሽሯል 

*ተጫዋቾቹ ወደ ስራ እንዲመለሱ ተወስኗል

*ለተጫዋቾቹ ያልተከፈለ ደመወዝ በሙሉ ይህ ውሳኔ ክለቡ ከደረሰው በ10 ቀናት ውስጥ እንዲከፈል ወስኗል ።